መጽሐፍ
መጽሐፍ
رسالة واحدة فقط!
አንዲት መልዕክት ብቻ! ዶ/ር ናጂ ቢን ኢብራሂም አል‐ዐርፈጅ መታሰቢያነቱ በእውነትና በኢኽላስ ትክክለኛዋን እውነታ ለሚፈልጉ እና አስተዋይ አዕምሮ ላላቸው ይሁን።
الإبداع في كمال الشّرع وخطر الابتداع
رسالة قيمة تبين أن كل من ابتدع شريعة في دين الله ولو بقصد حسن فإن بدعته هذه مع كونها ضلالة تعتبر طعنا في دين الله - عز وجل -.
وجوب العمل بالسنة وكفر من أنكرها
رسالة لطيفة تبين أهمية الالتزام بسنة النبي محمد صلى الله عليه وسلم وبيان كفر من ينكرها. تبدأ بالتأكيد على أن مصادر التشريع الإسلامي تعتمد على القرآن الكريم وسنة النبي محمد صلى الله عليه وسلم وإجماع علماء الأمة. تشرح الرسالة كيف أن القرآن وسنة النبي متلازمان، وتؤكد على ضرورة اتباع السنة لفهم وتطبيق أحكام الشريعة. يُستدل فيها بآيات القرآن وأحاديث النبي العدنان وشهادات من الصحابة والتابعين، لإثبات حجية السنة وأهمية التمسك بها. تُختتم الرسالة بتذكير المسلمين بضرورة طاعة الرسول والابتعاد عن مخالفة سنته لتحقيق الهداية والرحمة من الله جل جلاله.
ትክክለኛ ዐቂዳ እና ተቃራኒው እንዲሁም እስልምናን የሚያፈርሱ ነገሮች
ጸሐፊ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው መቅድም ምስጋና ሁሉ ለብቸኛው አላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰለላትና ሰላም ከእሳቸው በኋላ ነብይ የሌለ በሆኑት ነብይ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ይስፈን።
ስለ እስልምና አጭር ገለፃ፤ በተከበረው ቁርአን እና በነብያዊ ሐዲሥ በመጣበት መልኩ
እስልምና ይህ እስልምናን አጠር ባለ መልኩ የሚያስተዋውቅና የሚዳስስ አሳሳቢ መጽሐፍ ነው። መሰረታዊ ምንጮች ከሆኑት ከቅዱስ ቁርአን እና ከነብያዊ ሐዲሥ በመመርኮዝ ስለ (እስልምና) አሳሳቢ መሰረቶቹ፣ ስለ አስተምህሮቱ እንዲሁም ስለ መልካምነቱ የሚዳስስ አሳሳቢ ፅሁፍ ሲሆን፤ ኪታቡ ሙስሊምንም ይሁን ከሙስሊም ውጭ ያለ፤ በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ የሚገኝ፤ በየትኛውም መስክም ይሁን በየትኛውም ሁኔታ የሚገኝን ለአቅመ ሃላፊነት የደረሰን ሁሉ የሚመለከት አሳሳቢ ኪታብ ነው። (ከተከበረው ቁርአንና ከነብያዊ ፈለግ ማስረጃዎችን ያካተተ ቅጂ) 1- እስልምና ወደ ሰው ልጆች ሁሉ የተላከ የአላህ መልዕክት ነው። እንዲሁም ዘውታሪ የሆነ አምላካዊ የመጨረሻ መልዕክቱም ነው። እስልምና ወደ ሰው ልጆች ሁሉ የተላከ የአላህ መልዕክት ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።} (ሰባእ፡ 28) ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ {(ሙሐመድ ሆይ!)፡-…
የእስልምና የመጀመሪያ ቀኔ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው መግቢያ ምስጋና ነብዩ ሙሐመድን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለዓለማት እዝነት አድርጎ ለላከው አላህ የተገባ ነው። ከአላህም በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን፣ ብቸኛና በምንም ተጋሪ የሌለው መሆኑንም እመሰክራለሁ። የመጀመሪያዎቹም የመጨረሻዎቹም (ፍጥረታት ሁሉ) አምላክ እርሱው ነው። የነብያትም የመልዕክተኞችም መደምደሚያ የሆኑት ነብያችን ሙሓመድም -የአላህ ሶለዋትና ሰላም በርከት ብሎ እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ይስፈንባቸውና- የአላህ ባሪያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ። ከዚህም በማስከተል፦ ማንኛውም ሰው ደስታን ፈላጊ ነው፤ ታዲያ አንዳንዶቹ ይህ ደስታ ገንዘብ በመሰብሰብ የሚገኝ እንደሆነ ያስባሉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከዝና ጥላ ስር እየፈለጓት ይገኛሉ፤ አንዳንዶቹም እርሷን በከፍተኛ ማህበራዊ ክብር ላይ (እንዳለች አድርገው) ይመለከቷታል፤ ከዚህም ውጭ እነዚህን በመሳሰሉ በዱኒያ መጠቃቀሚያዎች ውስጥ የሚያስቡም አሉ፤ ተጨባጩ የሚያስረዳው እውነታ ግን እነዚህን ነገሮች ካገኙት…
በቁርኣን እና በነብያዊ ሓዲሥ በመጣው መሰረት ስለ ኢስላም አጠር ያለ መልዕክት።
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። እስልምና (ማስረጃ አልባ ቅጂ)[1] ለዚህ ፅሁፍ እያንዳንዱ ሃሳብ በተከበረው ቁርኣናዊ እና ነብያዊ ሐዲሥ ማስረጃ በተሟላ መልኩ ሌላ ቅጂ ያለ ሲሆን በተከታዩ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ፦ https://islamhouse.com/ar/books/283007 አጠር ባለ መልኩ እስልምናን ስለ ማስተዋወቅ፣ ስለ አሳሳቢ መሰረቶቹ፣ ስለ አስተምህሮቱ እንዲሁም ስለ መልካምነቱ መሰረታዊ ምንጮቹ ከሆኑት ቅዱስ ቁርኣን እና ነብያዊ ሓዲሥ በመመርኮዝ የሚዳስስ አሳሳቢ ፅሁፍ ሲሆን፤ ፅሁፉ ሙስሊምንም ይሁን ከሙስሊም ውጭ ያለውን ለአቅመ ሃላፊነት (አዳም ወይም ሄዋን) የደረሰ በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ የሚገኘውን በየትኛውም መስክም ሁኔታም የሚገኝን ሁሉ የሚመለከት ፅሁፍ ነው። 1. እስልምና ወደ ሰው ልጆች ሁሉ የተላከ ዘላለማዊ የሆነ አምላካዊ የአላህ መልዕክት ነው።
ጧትና ማታ የሚባሉ ዚክሮች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ (አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡) (አያቱል ኩርሲይ አል በቀራህ፡ 255) (መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲሆኑ) አመኑ፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» አሉም። * አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ…
ማን ነው የፈጠረኝ? ለምንስ ፈጠረኝ?
ሁሉም ነገር ፈጣሪ እንዳለ ይጠቁማል ሰማያትንና ምድርን፣ በውስጣቸውም ያለውን ማንም ሊያካብባቸው የማይቻሉ የሆኑትን ትላልቅ ፍጡራንን የፈጠራቸው ማን ነው? ይህን በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ፍፁም የረቀቀ የሆነውን ስርዓት የዘረጋው ማን ነው? የሰውን ልጅ መስሚያ፣ መመልከቻና አዕምሮ ለግሶ፤ ዕውቀትን በመፈለግ እውነታ ላይ እንዲደርስ ያስቻለውስ ማን ነው? ይህንን በሰውነትዎም በሕያዋን ፍጥረታት አካላትም ውስጥ ያለውን ይህንን የረቀቀ አሠራር እንዴት ይገልፁታል!? ማንስ ፈጠረው? ይህ ታላቅ አጽናፈ ዓለም ረቂቅ በሆነ መልኩ የሚቆጣጠረውን ስርዓት ይዞ እንዴት ለዚህ ሁሉ ዓመታት ወጥ እና የተረጋጋ ሊሆን ቻለ?
እስልምና የአላህ መልክተኞች ሃይማኖት ነው።
እስልምና ማለት አጽናፈ ዓለሙን ለፈጠረውና ላስተናበረው አላህ በመውደድና በማላቅ እጅ መስጠትና መታዘዝ ማለት ነው። የእስልምና መሰረቱ በአላህ ማመን ነው። እርሱ ፈጣሪ መሆኑን፤ ከርሱ ውጪ ያሉት ባጠቃላይ ፍጡር መሆናቸውን ማመን፤ እርሱ ብቸኛ አምልኮ የሚገባውና አጋር የሌለው መሆኑንና ከርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ማመን ነው። እስልምና ከርሱ ውጭ ያለው ሃይማኖት አላህ ከሰዎች የማይቀበለው የሆነ ብቸኛው ሃይማኖት ነው። እስልምና ሁሉም ነቢያቶች ሰላም ይስፈንባቸውና ይዘውት የመጡት ሃይማኖት ነው። ከእስልምና መሰረቶች መካከል በሁሉም መልዕክተኞች ማመን እና አላህ ትእዛዙን ለባሮቹ እንዲያስተላልፉ መልእክተኞችን እንደላከ እና መጽሐፎችን እንዳወረደላቸው ማመን ነው። የመጨረሻው መልዕክተኛም ሙሐመድ ሰላም ይስፈንባቸውና ናቸው። ከርሳቸው በፊት የነበሩትን የመልክተኞች ህግጋት በሚሽርና በመለኮታዊ ህግ ልኳቸዋል። በታላላቅ ተዓምራትም አግዟቸዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቁ የዓለማት ጌታ ንግግር የሆነው የተከበረው ቁርኣን ነው። የሰው ልጅ…
እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ጌታህ ማን ነው? ይህ በፍጥረተ ዓለሙ ውስጥ ትልቁ ጥያቄ ነው። ማንኛውም ሰው መልሱን ማወቅ ያለበት በጣም አስፈላጊው ጥያቄም ነው። ጌታችን ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ ከሰማይም ውኃን ያወረደ፤ በርሱም ለእኛና ለእንስሶች ምግብ ይሆነን ዘንድ ፍራፍሬና ዛፎችን ያወጣ (ያበቀለበት) ነው። ጌታችን እኛን የፈጠረን፤ አባቶቻችንንም የፈጠረ፤ ሁሉንም ነገር የፈጠረው እርሱ ነው። ሌሊትንና ቀንን ያደረገም እርሱ ነው፤ ሌሊትን የመኝታና የዕረፍት ጊዜ ቀኑን ደሞ ሲሳይና ቀለብን መፈለጊያ ጊዜ ያደረገ ጌታ ነው። ጌታችን ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትንና ባሕሮችን ያገራልን የምንበላባቸውንና ከወተታቸውም ከፀጉራቸውም የምንጠቀምባቸውን እንስሳትንም ያገራልን ጌታ አላህ ነው። የዓለማቱ ጌታ መገለጫ ባህሪዎች ምንድን ናቸው?
የነቢዩ ﷺ ሰላት አሰጋገድ
የተከበሩ ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) "የነቢዩ ﷺ የሶላት አሰጋገድ" የተሰኘውን መጽሐፍ ትክክለኛ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ፤ በቀላል ቋንቋና በጥንቁቅ አካሄድ አጠቃልለው አዘጋጅተውታል። የመጽሐፉ ዋና ዓላማ አንድ ሙስሊም በሶላቱ ውስጥ መመሪያ እንዲሆነው ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሸይኹ የሶላትን ማዕዘናት (አርካን)፣ ሱናዎችና አጠቃላይ ሥርዓቱን ከውዱእ አንስቶ እስከ ማሰላመት (ተስሊም) ድረስ በግልጽ አስቀምጠዋል። ማስረጃን ከማብራሪያ ጋር በማጣመር በዚህ ታላቅ የአምልኮ (ዒባዳ) ዘርፍ ነብዩን ﷺ ሙሉ በሙሉ መከተል እንደሚያስፈልግ ጥሪ ያቀርባሉ።
በቁርኣንና ሐዲሥ መሰረት የተዘጋጀ የበርካታ የሐጅ፣ የዑምራና የዚያራ ጉዳዮች ማረጋገጫና ማብራሪያ
መጽሐፉ በቁርኣንና ሐዲሥ መሰረት የሐጅን፣ የዑምራንና የጉብኝትን ህግጋት፣ እንዲሁም የሐጅና ዑምራን ግዴታዎች፣ በኢሕራም ወቅት ያሉ ክልከላዎችንና የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ የመዘየር ስነ ስርዓት ያብራራል፤ በእነዚህ የአምልኮ ሥርዓቶች ውስጥ ከሚፈጸሙ ቢድዐዎችም ያስጠነቅቃል።
የጉዞ ስነስርዓትና ህግጋቶቹ
ምስጋና የአለማት ጌታ ለሆነው አላህ የተገባ ነው። ሶላትና ሰላም በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ሁሉ ይስፈን። በመቀጠልም፦ ይህ የጉዞ ስነስርዓትና ህግጋትን በተመለከተ የሚያትት አጠር ያለ መልዕክት ነው። አንድ ተጓዥ አብዛኛው ጊዜ የሚያስፈልጉትን ጉዳዮች ለማብራራትም ጥረት አድርገናል። አላህን ብቻ ለተከበረው ፊቱ ጥርት ተደርጎ የተዘጋጀ እንዲያደርግልንና ለመላው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ጠቃሚ እንዲያደርግልን እንጠይቀዋለን። የመጀመሪያው: የጉዞ ስነስርዓት
የዑምራ አፈፃፀምና ህግጋት አጠር ያለ ማብራሪያ
ምስጋና ሁሉ የአለማት ጌታ ለሆነው አላህ የተገባ ነው። የአላህ ሶላትና ሰላም በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይስፈን። በመቀጠልም፦ ይህ መልዕክት የዑምራን አፈፃፀም፣ ህግጋትና ስነ ስርዓት አጠር ባለ መልኩ የሚያብራራ ነው። በዚህም አንድ ዑምራ አድራጊ በአብዛኛው የሚያስፈልገውን ለማብራራት ጥረት አድርገናል። አላህን ለተከበረው ፊቱ ጥርት ተደርጎ የተዘጋጀ እንዲያደርግልንና ለመላው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ጠቃሚ እንዲያደርግልን እንጠይቀዋለን።
የዑምራ አፈጻጸም
በሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) የተዘጋጀችው «የዑምራ አፈጻጸም» የተሰኘችው ትንሽ መጽሐፍ አንድ ሙስሊም የአምልኮ ሥርዓቱን አላህን ፈርቶና ተመስጦ (ኹሹዕ) እንዲሁም በቀላሉ እንዲፈጽም የሚረዳ ተግባራዊ መመሪያ ትሆን ዘንድ የዑምራን ሥነ-ስርዓቶች በግልጽና በቀላል አቀራረብ ታብራራለች። መጽሐፏ በእያንዳንዱ እርከን ላይ የሚባሉ የተረጋገጡ ዱዓዎችንና ዚክሮችንም አካታለች።
በሐጅ፣ በዑምራና በዚያራ ወቅት የሚስተዋሉ ተቃርኖዎች
ከዑምራ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስህተቶችና ተቃርኖዎች የመጀመሪያው: ሰዎች በኢሕራም ወቅት የሚሰሯቸው ስህተቶችና ተቃርኖዎች: 1. ኢህላልን መተው (ድምፅን ከፍ አድርጎ ተልቢያ አለማለት)። ይህ ማለት አንድ ሰው ኢሕራም ሲጀምር ሊፈጽመው ያሰበውን የሐጅ ወይም የዑምራ አይነት ድምፁን ከፍ አድርጎ አለመግለጹ ነው። ሱናው ግን ድምፅን ከፍ አድርጎ መናገር ነው።
የሐጅ አፈፃፀም አጭር ማብራሪያ
ምስጋና የአለማት ጌታ ለሆነው አላህ የተገባ ነው። ሶላትና ሰላም በነብያችን ሙሐመድ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸውም ላይ ሁሉ ይስፈን። ከዚህ በመቀጠል:- ይህ የሐጅን አፈፃፀም የሚያብራራ አጠር ያለ መልዕክት ነው። አንድ ሐጅ አድራጊ በአብዛኛው ሊፈፅመው የሚገባውን ለማብራራት ጥረት አድርገናል። ለተከበረው አላህ ጥርት ተደርጎ የተዘጋጀና ለአጠቃላይ ለሙስሊሙ ማህበረሰብም ጠቃሚ እንዲያደርግልን አላህን እንጠይቀዋለን። መግቢያ
የረመዳን ወርን የተመለከቱ ጥያቄዎችና መልሶች ለህፃናት እና ለአዋቂዎች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው መግቢያ ምስጋና ሁሉ የረመዳንን ወር ከሌሎች ወራትና ቀናት በብዙ ደረጃዎች ላላቀውና ልዩ ላደረገው አላህ ነው። የአላህን ሰላትና ሰላም በሙሐመድ ኢብኑ ዐብደላህ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ እንዲሰፍን እንለምናለን። ከዚህ በመቀጠል፦ ይህ ስለ ረመዳን ወር የሚያትት ጥያቄና መልስ የተዘጋጀው ለልጆች ሲሆን አዋቂዎችንም ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ነው። የተባረከውን የረመዳን ወር አስመልክቶ ግዴታ የሚሆኑ፣ ተወዳጅ የሆኑና በረመዳን ወር ሊፈፀሙ የሚገቡ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሣል። አስተማሪው የሚፈልገውንና ለልጁ እና ለእድሜው ተስማሚ የሆነውን ይመርጣል።
ሀድይ፣ ኡዱሒያና እርድን የተመለከቱ ህግጋት
የሀድይ፣ የኡድሒያና የአስተራረድ ህግጋትን በተመለከተ የተዘጋጀ አጠር ያለች መፅሀፍ ስትሆን አንድ ሙስሊም በሃይማኖቱ ጉዳይ ላይ አዋቂ ይሆን ዘንድ ስለ ሀድይ፣ ኡድሒያና አስተራረድ በዋናነት ሊያውቅ የሚያስፈልጉትንም ህግጋቶች አካታለች።
እኔ ሙስሊም ነኝ
ይህ ጽሑፍ የኢስላምን ምንነት፣ ሙስሊም ማን እንደሆነ፣ እንዲሁም እውነተኛ ሙስሊም እንዴት መሆን እንደሚቻል ያብራራል። በተጨማሪም የኢስላምን መልካም ገጽታዎች፤ ምጡቅ ሥነ ምግባርና ሥርዓቶች፤ የሴትን ልጅ ክቡር ቦታ እንዲሁም የቅርብ ዘመድ፤ የጎረቤትና የማኅበረሰብ መብቶችን አካቷል። ኢስላም ወደ መልካም ምግባር ሁሉ እንደሚያዝና ጥሪ እንደሚያደርግ፤ ከክፉ ምግባር ሁሉ ደግሞ እንደሚከለክልም ይገልጻል።
የሒራን ዋሻ መዘየር
የሒራን ዋሻ መዘየር የሚለው መጽሐፍ ይህ ስፍራ የነቢይነት ተልዕኮ መነሻና የመጀመሪያው የተከበረው ቁርአን አናቅፆች መውረጃ ስፍራ መሆኑን የሚገልፅ ነው። እንዲሁም መካ ውስጥ እንዲሰሩ የተደነገጉ አምልኮዎች የሚፈፀሙት በመስጂደል ሐራም ላይና ለሐጅ በተወሰኑ ልዩ ስፍራዎች ላይ ብቻ የተገደበ መሆኑንና እንደ ሒራ ዋሻ ባሉ ስፍራዎች እርዳታን መጠየቅ፣ በረከትን መጠየቅና ሌሎችም ያልተደነገጉ መጤ አምልኮዎችን ሁሉ መፈፀምን በመተው ላይ ግንዛቤን የሚሰጥ መጽሐፍ ነው። በተጨማሪም የነቢዩን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱና ከመፃረር ያስጠነቅቃል። መጽሐፉ ለሁሉም አማኝ መልካም አርአያችን የሆኑትን የአላህን መልክተኛ በመከተል ለአላህ ብቻ ጥርት ወዳለችው አላህን በአምልኮ ወደመነጠልም ይጣራል።
የኢስላም መልዕክተኛ የሆኑት ሙሐመድ የአላህ ሶላት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን
«የኢስላም መልዕክተኛ የሆኑት ሙሐመድ የአላህ ሶላት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን» የሚለው መጽሐፍ የነቢዩ ሙሐመድን (የአላህ ሶላት እና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘራቸውን፣ አስተዳደጋቸውን፣ የተባረከው ትዳራቸውን፣ የወሕይ አወራረድን፣ የመጨረሻ መልዕክታቸው አጀማመርን ጨምሮ ስለ ህይወታቸው የሚያብራራ መጽሐፍ ነው። በተጨማሪም የነቢይነታቸውን ተአምርና የእውነተኝነታቸውን ምልክትም ይገልፃል። እንዲሁም: ይዘውት የመጡት ሸሪዓ የሰው መብት እንዲጠበቅ እና እንዲከበር የነበረውን ሚናም ያብራራል። እርሳቸውን የተቃረኑ አካላት በርሳቸው ላይ የነበራቸውን አቋም እና ለርሳቸው የሰጡትን ምስክርነትም ለሰዎች መሪ እና ስለ ፈጣሪ አሃዳዊነት ተጣሪ ያደረጋቸውን የላቀ ስብዕና ከመተንተን ጋር የሚቀርብበት መጽሐፍ ነው።
የነቢዩ መስጂድ ትሩፋቶችና ስነ ስርዓት፤ የነቢዩን (ﷺ) ቀብርና የሁለቱ ባልደረቦቻቸውን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) ቀብሮች የመዘየር ህግጋት
መጽሐፉ የነቢዩን ﷺ መስጂድ ትሩፋቶችና የመዘየር ስነ ስርዓቱን እንዲሁም የነቢዩን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቀብርና የሁለቱ ባልደረቦቻቸው (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) ቀብሮችን የመዘየር ስነ ስርዓት ያብራራል፤ በጉብኝቱ ወቅት የእርጋታን፣ የንፅህናንና ከቢድዐ ድርጊቶች የመራቅን አስፈላጊነትም ያጠነክራል።