Skip to content
الإسلام دين رب العالمين

الإسلام دين رب العالمين

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው እስልምና የዓለማት ጌታ ሃይማኖት ጌታህ ማን ነው? ይህ በፍጥረተ ዓለሙ ውስጥ ትልቁ ጥያቄ ነው። ማንኛውም ሰው መልሱን ማወቅ ያለበት በጣም አስፈላጊው ጥያቄም ነው። ጌታችን ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ ከሰማይም ውኃን ያወረደ፤ በርሱም ለእኛና ለእንስሶች ምግብ ይሆነን ዘንድ ፍራፍሬና ዛፎችን ያወጣ (ያበቀለበት) ነው። ጌታችን እኛን የፈጠረን፤ አባቶቻችንንም የፈጠረ፤ ሁሉንም ነገር የፈጠረው እርሱ ነው። ሌሊትንና ቀንን ያደረገም እርሱ ነው፤ ሌሊትን የመኝታና የዕረፍት ጊዜ ቀኑን ደሞ ሲሳይና ቀለብን መፈለጊያ ጊዜ ያደረገ ጌታ ነው። ጌታችን ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትንና ባሕሮችን ያገራልን የምንበላባቸውንና ከወተታቸውም ከፀጉራቸውም የምንጠቀምባቸውን እንስሳትንም ያገራልን ጌታ አላህ ነው። የዓለማቱ ጌታ መገለጫ ባህሪዎች ምንድን ናቸው?

0%
Font size