Skip to content
مقدمة وغلاف المنتقى من موسوعة الأحاديث النبوية

مقدمة وغلاف المنتقى من موسوعة الأحاديث النبوية

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በኾነው እጀምራለሁ መቅድም ምስጋና ባጠቃላይ ለአለማት ጌታ ለአሏህ የተገባ ነው። የአሏህ ውዳሴና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው እንዲሁም እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ በተከተላቸው ላይ ሁሉ ይስፈን። በመቀጠል: አንድ ሙስሊም ከቁርአን ቀጥሎ በማንበቡም፣ በመማሩም፣ በማስተንተኑ በኩልም፣ በመተግበሩ ረገድም ትልቁን ትኩረት ሊቸረው የሚገባው ጉዳይ ቢኖር የረሱል ‐ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ‐ ሱናቸውን ነው። ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) የአሏህ ውዳሴና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «ሰዎች ሆይ! አጥብቃችሁ ብትይዙት መቼም የማትጠሙበት የሆነን ነገር በመካከላችሁ ትቼላችኋለሁ: ይኸውም የአሏህ ኪታብ እና የነቢዩ ሱና ነው።» ኢማም ማሊክ ዘግበውታል። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል: {መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡} [አል‐ሐሽር: 7] ለዛም…

0%
Font size