Skip to content

"ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን

ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡

"ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን የተቸገረ ካጋጠመህ እለፈው።' (ሞተና) አላህንም ተገናኘ፤ አላህም ይቅር አለው።"

«كان رجلٌ يُدَايِنُ الناسَ، فكان يقول لفتاه: إذا أتيتَ مُعسِرًا فتجاوز عنه، لعل اللهَ يَتجاوزُ عنا، فلقي اللهَ فتجاوز عنه».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰዎች ጋር በመበዳደር የሚንቀሳቀስ ወይም በዱቤ የሚሸጥላቸው ስለሆነ ሰው ተናገሩ። ለሰዎች ያበደረውን ብድር ለሚቀበልለት ሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ "ተበዳሪ ዘንድ ስትሄድ እዳውን መክፈል ተስኖት ካገኘኸው እለፈው" ይህም የሚከፍልበትን ፋታ በመስጠት፣ እዳውን በመፈለግ ላይ ችክ ባለማለት ወይም ጥቂት ቢጎድልም ያለውን በመቀበል ሊሆን ይችላል። ይህንንም የሚያደርገው አሏህ የእርሱንም ወንጀል እንዲያልፍለትና ይቅር እንዲለው ከመከጀል አኳያ ነበር። በሞተም ጊዜ አሏህም ማረው፤ ወንጀሉንም ይቅር አለለት።

የቃላት ፍቺ

يداين: يكثر من التعامل مع الناس بالدين.

فتاه: غلامه الذي يكلفه بالعمل.

أتيت معسرًا: لمطالبته بما عليه.

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ከሰዎች ጋር ባለ መስተጋብር መልካሙን መዋል፣ ይቅር ማለትና ሰው ሲቸግረው ብድሩን ማለፍ አንድ ባርያ በቂያማ እለት ከሚድንባቸው ትላልቅ ሰበቦች መካከል እንደሆነ እንረዳለን።

ለፍጡራን በጎ መዋል፣ ለአሏህ ስራን ጥርት ማድረግና እዝነቱንም መከጀል ለወንጀል መሀርታን ከሚያስገኙ ሰበቦች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (4/ 176) (3480).

ሶሒሕ ሙስሊም (3/ 1196) (1562).

ተጨማሪ (9)

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (2/ 458).

التنوير شرح الجامع الصغير.

للصنعاني (8/ 123).

كنوز رياض الصالحين.

لمجموعة من الباحثين (16/ 402).

مرقاة المفاتيح شرح مشكاة المصابيح.

للقاري (5/ 1953).

نزهة المتقين شرح رياض الصالحين (2/ 945).