Skip to content

"የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

"የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ ጉቦ ሰጪንም ተቀባይንም ረገሙ።"

لَعَنَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ الرَّاشِيَ وَالْمُرْتَشِيَ فِي الْحُكْمِ.

ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጉቦ በሚሰጥ፣ በሚቀበልና በሚበላ ሰው ላይ ከአላህ እዝነት እንዲርቅና እንዲባረር ዱዓ አደረጉበት። ከዚህም መካከል ጉቦ ሰጪው ያለአግባብ ወደ ፍላጎቱ ለመዳረስ ሲል ለዳኞች በተሾሙበት ፍርድ እንዲያዘነብሉ (ኢፍትሃዊ እንዲሆኑ) የሚሰጠው ጉቦ እዚህ ውስጥ ይመደባል።

የቃላት ፍቺ

لعن: حقيقة اللعن الدعاء بالطرد والإبعاد عن رحمة الله تعالى.

الراشي: هو دافع الرشوة.

المرتشي: آخذ الرشوة.

في الحكم: في القضاء.

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ጉቦ መስጠት፣ መቀበል፣ አገናኝ መሆንና ተባባሪ መሆን በተሳሳተ ነገር ላይ መተባበር ስለሆነ ክልክል ነው።

የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጉቦ ተቀባይንም ሆነ ሰጪን ስለረገሙ ጉቦ ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ነው።

ጉቦ በዳኝነትና ፍርድ ላይ ከሆነ የተከናወነው በውስጡ አላህ ካወረደው ፍርድ ውጪ በግፍ መፍረድም ስላለው ከባድ ወንጀልና አደገኛ ኃጢአት ይሆናል።

ማጣቀሻዎች

ሱነን ቲርሚዚ (3/ 15) (1336).

ሙስነድ አሕመድ (15/ 8) (9023).

ተጨማሪ (8)

توضيح الأحكام مِن بلوغ المرام.

للبسام (7/ 188).

فتح ذي الجلال والإكرام شرح بلوغ المرام.

لابن عثيمين (6/ 172).

منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (9/ 450).

سبل السلام شرح بلوغ المرام.

للصنعاني (2/ 577).