Skip to content

'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።

ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:

'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።' ከዚያም {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"} [ጋፊር: 60] የሚለውን አነበቡ።"

«الدُّعَاءُ هُوَ الْعِبَادَةُ»، ثُمَّ قَرَأَ: «{وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ} [غافر: 60]».

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አምልኮ እንደሆነ ተናገሩ። በዱንያና በአኺራዊ ጉዳዮች የሚጠቅመውን ነገር እንዲሰጠውና የሚጎዳውን ነገር እንዲከላከልለት አላህ የሚጠየቅበት ልመናዊ ዱዓም ይሁን፤ ማንኛውም ውጫዊና ውስጣዊ ንግግርም ተግባርም አላህ የሚወዳቸውና የሚያስደስተው ልባዊ፣ አካላዊና ገንዘባዊ አምልኮዎችን የሚያደርጉበት አምልኳዊ ዱዓእም ቢሆን ያው ነው። እነዚህ የዱዓእ አይነቶችም ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርገው መፈፀማቸው ግዴታ ነው። ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለዚህ ንግግራቸው የአላህን ንግግር ማስረጃ አደረጉ። አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"}

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ዱዓእ የአምልኮ መሰረት በመሆኑ ከአላህ ውጪ ለሆነ መስጠት አይፈቀድም።

ዱዓእ እውነተኛ ባርነትን፣ የጌታን መብቃቃትና ችሎታ እውቅና መስጠትን እና የባሪያን ወደ አላህ ፈላጊነቱን ሰብስቦ የያዘ ነው።

ከአላህ አምልኮ በመኩራትና ዱዓእን በመተው ፍዳ ዙሪያ ብርቱ ዛቻ መምጣቱን እንረዳለን። አላህን ከመለመን የሚኮሩ ሰዎች ጀሀነም የተናነሱና የተዋረዱ ሆነው ይገባሉ።

ማጣቀሻዎች

ሱነን አቡዳውድ (2/ 603) (1479).

ሱነን ቲርሚዚ (5/ 292) (3247).

ሱነን ኢብኑ ማጀህ (5/ 5) (3828).

ሙስነድ አሕመድ (30/ 297) (18352).

ተጨማሪ (8)

توضيح الأحكام من بلوغ المرام.

للبسام (7/ 546).

منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (10/ 416).

فتح ذي الجلال والإكرام.

لابن عثيمين (6/ 480).

سبل السلام بشرح بلوغ المرام.

للصنعاني (2/ 707).