Skip to content

ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'"

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች:

"ሰዎች የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለጠንቋዮች ጠየቁ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነርሱ 'ምንም አይደሉም።' በማለት መለሱ። እነሱም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳንድ ጊዜ አንድ ነገር ተናግረው እውነት ይሆናል።' አሉ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ ' ይህቺ ጂኒ የሚሰርቃት የእውነት ንግግር ናት። በወዳጁ ጆሮ ውስጥም ዶሮ ጩኸቷን እንደምትደጋግመው ይደጋግምለታል። በዚህች እውነት ውስጥም ከመቶ ውሸት በላይ ይቀላቅሉበታል።'"

سَأَلَ أُنَاسٌ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الْكُهَّانِ، فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَيْسُوا بِشَيْءٍ» قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، فَإِنَّهُمْ يُحَدِّثُونَ أَحْيَانًا بِالشَّيْءِ يَكُونُ حَقًّا، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «تِلْكَ الْكَلِمَةُ مِنَ الْحَقِّ يَخْطَفُهَا الْجِنِّيُّ فَيَقُرُّهَا فِي أُذُنِ وَلِيِّهِ قَرَّ الدَّجَاجَةِ، فَيَخْلِطُونَ فِيهَا أَكْثَرَ مِنْ مِائَةِ كَذْبَةٍ».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለወደፊት ስለሚከሰቱ የሩቅ ሚስጥራት ስለሚናገሩ ሰዎች ተጠየቁ። እሳቸውም: ቦታ አትስጡት ፤ ንግግራቸውን አትያዙ፤ ጉዳያቸው አያሳስባችሁ አሉዋቸው። ሶሐቦችም "በእንዲህ ወርና በእንዲህ ቀን" ብለው የሩቅ ሚስጥር ጉዳይ እንደሚከሰት እንደሚናገሩና እንደተናገሩት ገጥሞ መከሰቱን አይነት ንግግራቸው አንዳንድ ጊዜ ተጨባጩን የሚገጥም መሆኑን ተናገሩ። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም እንዲህ ብለው መለሱላቸው "ጂኖች ከሰማይ የሚሰሙትን ወሬ በመስረቅ ወደ ጠንቋይ ወዳጆቻቸው አውርደው የሰሙትን ይነግሯቸዋል። ከዚያም ጠንቋዩ ከሰማይ በሰማው ላይ መቶ ውሸት ይጨምርበታል።"

የቃላት ፍቺ

يخْطفُها: يأخذها بسرعة.

فَيَقُرُّهَا في أُذُنِ: يلْقِيهَا على مسَامِع.

قرَّ الدجاج: صوتها عند مخاطبة دجاجة أخرى.

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ጠንቋዮችን ማመን መከልከሉን ፤ አንዳንድ ጊዜ እውነት ቢናገሩ እንኳ የሚናገሩት ነገር ውሸትና ቅጥፈት መሆኑን እንረዳለን።

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመላካቸው ምክንያት ከተወርዋሪ ኮኮብ አምልጦ ወሬ የሰረቀ ጂን ካልሆነ በቀር ሰይጣናት ከወሕይም ይሁን ሌላ እንዳይሰሙ ሰማይ ተጠብቃለች።

ጂኖች ከሰው የሆነ ወዳጅ እንደሚይዙ እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (8/ 47) (6213).

ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 1750) (2228).

ተጨማሪ (9)

نزهة المتقين (2/ 1143).

كنوز رياض الصالحين.

لمجموعة من الباحثين (17/ 557).

بهجة الناظرين.

لسليم الهلالي (3/ 177).

مرقاة المفاتيح شرح مشكاة المصابيح.

لعلي القاري (7/ 2904).

شرح رياض الصالحين.

لابن عثيمين (6/ 404).