Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 6 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
እርሱ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ እንዲሁም በቂረአቴ መካከል አዘናጋኝ። በኔ ላይም ያለባብስብኛል።" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!" አሉት። እርሱም "ይህንን ፈፀምኩ አላህም አስወገደልኝ።" አለ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን እሱን ከመናገር ይልቅ አመድ መሆን የሚያስደስተውን ነገር በነፍሱ ውስጥ ይሰማዋል።" እርሳቸውም፦ "አላሁ አክበር አላሁ አክበር የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ የመለሰው አላህ ምስጋና ይገባው።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና ነሳኢ በኩብራ ዘግበውታል።
እውነተኛና (ይዘውት በመጡትም ሁሉ) እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን) ነገሩን፦ "የአንዳችሁ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀንና ምሽት ይሰበሰባል። ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ የረጋ ደም ይሆናል፤ ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ ቁራጭ ስጋ ይሆናል፤ ከዚያም ወደርሱ መልዐክ ይላካል ፤ መልዐኩ አራት መልእክቶች ይታዘዛል፤ ሲሳዩን፣ የሞት ቀጠሮውን፣ ስራውንና እድለቢስ ወይም እድለኛ መሆኑን ይጽፋል። ከዚያም በውስጡ ነፍስ ይነፋበታል። አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ውሳኔ) ይቀድምና የእሳት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል። አንዳችሁ በርሱና በእሳት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከበላዩ ድምፅ ሰማና ራሱን ቀና አደረገ። እንዲህም አለ: "ይህ ዛሬ የተከፈተ የሰማይ በር ነው። ከዛሬ በቀርም ተከፍቶ አያውቅም።" ከተከፈተው በርም መልአክ ወረደ። ጂብሪልም እንዲህ አለ: "ይህ ወደ ምድር የወረደ መልአክ ነው። ከዛሬ በቀርም በጭራሽ ወርዶ አያውቅም" መልአኩም ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አለ: "ከአንተ በፊት ማንም ያልተሰጠው በሆነ ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለት ብርሃኖች አበስርሃለሁ። (እነርሱም) የመጽሐፉ መክፈቻ (ፋቲሓ) እና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎቹ ናቸው። ከነርሱም አንድም ፊደል አታነብም የሚሰጥህ ቢሆን እንጂ።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው። ከጭንቅላቱ በላይ የተወከለ መልአክ አለ። ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገለት ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክም "አሚን ላንተም ተመሳሳዩ አለህ።" ይለዋል።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።