Skip to content

"ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።"

ከዐብደላህ ቢን ሚሕሰን አልአንሷሪይ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ:

"ከናንተ መካከል ሰውነቱን ጤነኛ ሆኖ፤ በነፍሱና በቤተሰቡ ላይ ደህና ሆኖ፤ የእለት ቀለቡ እርሱ ዘንድ ኑሮ ያነጋ ሰው ዱንያን በሙሉ እንደተረከባት ይቁጠር።"

«مَنْ أَصْبَحَ مِنْكُمْ مُعَافى فِي جَسَدِهِ، آمِنًا فِي سِرْبِهِ، عِنْدَهُ قُوتُ يَوْمِهِ، فَكَأَنَّمَا حِيزَتْ لَهُ الدُّنْيَا».

ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።
ሐሰን ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከናንተ ከሙስሊሞች መካከል ሰውነቱን ከበሽታና ህመም ጤነኛና ደህና ሆኖ፤ በነፍሱ፣ በቤተሰቡ፣ በዘመዶቹና በመንገዱ ላይ ሁሉ ሳይፈራ ደህንነቱ የተጠበቀለት ሆኖ፤ እርሱ ዘንድ በቂ ሐላል የሆነ የቀን ቀለብ ኑሮት ያነጋ ሰው ዱንያ ባጠቃላይ ለርሱ እንደተሰበሰበችለት አምሳያ መሆኑን ተናገሩ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የሰው ልጅ ጤንነት፣ ደህንነትና ቀለብ የግድ እንደሚያስፈልገው መገለፁን እንረዳለን።

አንድ ባሪያ በነዚህ ፀጋዎች አላህን ማመስገንና ማወደስ እንደሚገባው እንረዳለን።

ከዱንያ ቸልተኛ በመሆንና በመብቃቃት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሱነን ቲርሚዚ (4/ 167) (2346).

ሱነን ኢብኑ ማጀህ (5/ 253) (4141).

ተጨማሪ (4)

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (1/ 570).

التنوير شرح الجامع الصغير.

لمحمد الصنعاني (10/ 110).