Skip to content

"ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"

ከዐብደላህ ቢን ቡስር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእስልምና ድንጋጌዎች በርግጥም በኛ ላይ በዙብን። አጥብቄ የምይዘውን ዋናውን በር ይንገሩን።" እርሳቸውም እንዲህ አሉ:

"ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"» በሌላ ዘገባ: በሙዓዝ ቢን ጀበል - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሐዲሥ እንደተላለፈው: ሙዓዝ እንዲህ አሉ: «"የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተለያየሁት የመጨረሻ ንግግሬ "ወደ አላህ እጅግ የሚያቃርበኝና መልካሙ ስራ ማንኛው ስራ ነው?" የሚል ነበር። እርሳቸውም: "ምላስህ አላህን ዓዘ ወጀል በማውሳት እርጥብ ሆኖ መሞትህ ነው።" በማለት መለሱልኝ።»

«لاَ يَزَالُ لِسَانُكَ رَطْبًا مِنْ ذِكْرِ اللَّهِ». وفي رواية: مِنْ حَدِيثِ مُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: آخِرُ مَا فَارَقْتُ عَلَيْهِ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ قُلْتُ: أَيُّ الأَعْمَالِ خَيْرٌ وَأَقْرَبُ إِلَى اللَّهِ؟ قَالَ: «أَنْ تَمُوتَ وَلِسَانُكَ رَطْبٌ مِنْ ذِكْرِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ».

ኢማሙ አሕመድ፣ ቲርሚዚይ፣ ኢብኑ ማጃህ እና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከደካማነቱ አንፃር ግዴታ ያልሆኑ አምልኮዎች እስኪያቅቱት ድረስ መብዛታቸው እንደተሰማው ስሞታ አቀረበ። ቀጥሎም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብዙ ምንዳ የሚያመጣለት የሆነን አጥብቆ የሚይዘውን ቀላል ስራ እንዲጠቁሙት ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታና ወቅት ምላሱ በ"ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ በ"ተሕሚድ" (አልሐምዱሊላህ)፣ ምህረት በመጠየቅ (አስተጝፊሩሏህ)፣ ዱዓ በማድረግና በመሳሰሉት አላህን በማውሳት ዘውትሮ ምላሱን ማንቀሳቀስና ማርጠብ እንዳለበት ጠቆሙት።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

አላህን በማውሳት ላይ መዘውተር ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።

ከአላህ ችሮታ መካከል ትልቁ ምንዳን ማግኛ መንገዶችን ማቅለሉ ተጠቃሽ ነው።

ባሮች በበጎና መልካም እጣ ፈንታቸው እንደሚበላለጡ እንረዳለን።

እንደ "ሱብሐነላህ"፣ "አልሐምዱሊላህ"፣ "ላኢላሃ ኢለላህ"፣ "አላሁ አክበር"ና ከዚህም ውጪ ያሉ አዝካሮችን ከቀልብ ጋር በማስተሳሰር በምላስ አላህን አብዝቶ ማውሳት የብዙ ግዴታ ያልሆኑ (ሱና) አምልኮዎችን ደረጃ ይይዛል።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሁሉም ጠያቂዎች የሚስማማቸውን መልስ እየጠበቁ መመለሳቸውን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሱነን ቲርሚዚ (5/ 318) (3375).

ሱነን ኢብኑ ማጀህ (4/ 707) (3793).

ሙስነድ አሕመድ (29/ 226) (17680).

ተጨማሪ (8)

جامع العلوم والحكم في شرح خمسين حديثا من جوامع الكلم.

لابن رجب الحنبلي (2/ 510).

التحفة الربانية في شرح الأربعين حديثًا النووية.

لإسماعيل الأنصاري (ص104).

فتح القوي المتين في شرح الأربعين وتتمة الخمسين.

للنووي وابن رجب (ص154).

الأحاديث الأربعون النووية وعليها الشرح الموجز المفيد.

لعبد الله بن صالح المحسن (ص93).