Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 52 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"
ሶሒሕ ነው። ኢማሙ አሕመድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ ኢብኑ ሒባን በሶሒሓቸው እና ሓኪም ዘግበውታል
"አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እንዲህ በማለት ወደ ጀነት ላከው። "ወደ ርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" ወደ እርሷ ተመልክቶ በመመለስ እንዲህ አለ፦ "በልቅናህ ይሁንብኝ ስለርሷ ማንኛውም ሰው ቢሰማ ከመግባት ወደኋላ የሚል የለም" አላህም በሷ ጉዳይ ትእዛዙን አስተላልፎ (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከበበች። በድጋሚ ጂብሪልን "ወደርሷ ሂድና ወደርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" አለው። ወደርሷ ተመለከተ፥ ድንገት (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከባ ተመለከታት። "በልቅናህ እምላለሁ! በርግጥም ማንም አይገባትም ብዬ ፈራሁ።" ብሎ ለአላህ መለሰ። አላህም፦ " ወደ እሳትና ለባለቤቶቿ በውስጧ ያዘጋጀሁትን ሂድና ተመልከት" በማለት አዘዘው። ጂብሪልም ወደርሷ ሲመለከት ያንጊዜ እሷ ከፊሏ ከፊሉን ሲበላ ተመለከተ። በመመለስም እንዲህ አለ "በልቅናህ እምላለሁ ማንም አይገባትም" አላህም በሷ ጉዳይ ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች እንድትከበብ አዘዘ። ቀጥሎም ደግመህ ወደርሷ ሂድና ተመልከት አለው ድንገት ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች ተከባ ወደርሷ ተመለከተ። "በልቅናህ እምላለሁ! ወደርሷ ከመግባት አንድም ከሷ አይድንም ይገባታል ብዬ ፈራሁ።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
"ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
"ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
«አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመምጣት እንዲህ አለ: "ምንዳንም መወደስንም ፈልጎ የዘመተ ሰው ለርሱ አላህ ዘንድ ምን እንዳለው ንገሩኝ?" የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመልሱ "ምንም የለውም!" አሉ። ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ጠየቃቸው የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመልሱ "ለርሱ ምንም የለውም!" ይሉ ነበር። ቀጥለውም "አላህ ለርሱ ፊት ብቻ ተብሎና ጥርት ተደርጎ የተሰራ ስራን ካልሆነ በቀር አይቀበልም።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ነሳኢይ ዘግበውታል
"በዝናባማና በድቅድቅ ጨለማ ምሽት የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኛን እንዲያሰግዱን ፈልገን ወጣን። አገኘኋቸውና 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። ቀጥለውም 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። አሁንም 'በል!' አሉኝ። እኔም ምን ልበል? አልኳቸው። እርሳቸውም 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
"በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'"
ሐሰን ነው። ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።»
በዘገባ ሰንሰለቶች ጥምረት ሐሰን የሆነ አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል