Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 87 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እንዲህ በማለት ወደ ጀነት ላከው። "ወደ ርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" ወደ እርሷ ተመልክቶ በመመለስ እንዲህ አለ፦ "በልቅናህ ይሁንብኝ ስለርሷ ማንኛውም ሰው ቢሰማ ከመግባት ወደኋላ የሚል የለም" አላህም በሷ ጉዳይ ትእዛዙን አስተላልፎ (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከበበች። በድጋሚ ጂብሪልን "ወደርሷ ሂድና ወደርሷና በውስጧ ለባለቤቶቿ ያዘጋጀሁትን ተመልከት!" አለው። ወደርሷ ተመለከተ፥ ድንገት (ለነፍስ) በሚከብዱ ነገሮች ተከባ ተመለከታት። "በልቅናህ እምላለሁ! በርግጥም ማንም አይገባትም ብዬ ፈራሁ።" ብሎ ለአላህ መለሰ። አላህም፦ " ወደ እሳትና ለባለቤቶቿ በውስጧ ያዘጋጀሁትን ሂድና ተመልከት" በማለት አዘዘው። ጂብሪልም ወደርሷ ሲመለከት ያንጊዜ እሷ ከፊሏ ከፊሉን ሲበላ ተመለከተ። በመመለስም እንዲህ አለ "በልቅናህ እምላለሁ ማንም አይገባትም" አላህም በሷ ጉዳይ ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች እንድትከበብ አዘዘ። ቀጥሎም ደግመህ ወደርሷ ሂድና ተመልከት አለው ድንገት ለስሜት በሚያስደስቱ ነገሮች ተከባ ወደርሷ ተመለከተ። "በልቅናህ እምላለሁ! ወደርሷ ከመግባት አንድም ከሷ አይድንም ይገባታል ብዬ ፈራሁ።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
"ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
"ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።"»
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
"(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
"ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁን) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።' አሏቸው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"አንድም በኔ ላይ ሰላምታን የሚያቀርብ የለም ለርሱ ሰላምታን እስክመልስ ድረስ አላህ ለኔ ነፍሴን የሚመልስልኝ ቢሆን እንጂ።"
ሰነዱ ሐሰን ነው። አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።