ኢስላም ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ልትመሰክር፣ ሰላት ደንብና ስርዓቱን ጠብቀህ ልትሰግድ፣ ዘካን ልትሰጥ ፣ ረመዷንን ልትፆምና ወደርሱ መንገድን ከቻልክም የአላህን ቤት ልትጎበኝ ሐጅ ልታደርግ ነው።
ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
ከዕለታት አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ሳለን ድንገት ልብሱ እጅግ በጣም ነጭ የሆነ፤ ፀጉሩ ደግሞ እጅግ በጣም ጥቁር የሆነ ሰውዬ ብቅ አለ። በሱ ላይ የጉዞ ምልክት አይታይበትም፤ ከኛ ውስጥም አንድም የሚያውቀው ሰው የለም፤ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጥቶ ተቀመጠ። ጉልበቱን ወደ ጉልበታቸው አስጠጋ፤ መዳፎቹንም በታፋዎቹ ላይ አደረገና "ሙሐመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ!" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ኢስላም ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ልትመሰክር፣ ሰላት ደንብና ስርዓቱን ጠብቀህ ልትሰግድ፣ ዘካን ልትሰጥ ፣ ረመዷንን ልትፆምና ወደርሱ መንገድን ከቻልክም የአላህን ቤት ልትጎበኝ ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉት። እሱም "እውነት አልክ!" አላቸው። "በሱ ተገረምን ይጠይቃቸዋልም (ጥያቄውን በትክክል እንደመለሱ) ያረጋግጥላቸዋልም።" ከዚያም፦ "ስለኢማን ንገሩኝ!" አላቸው። እሳቸውም "በአላህ፣ በመላእክቱ፣ በመጻሕፍቱ፣ በመልክተኞቹ፣ በመጨረሻው ቀንና በጥሩውም ሆነ መጥፎ ውሳኔዎቹም ልታምን ነው።" አሉት። እሱም "እውነት አልክ!" አላቸው። "ስለኢሕሳን (በጎ መስራት) ንገሩኝ!" አላቸው። እሳቸውም "አላህን ልክ እንደምታየው ሆነህ ልትገዛው ነው። አንተ ባታየው እንኳ እርሱ ያይሀልና።" አሉት። "ስለ ሰዓቱቱ (ቂያማ) ንገረኝ!" አላቸው። እሳቸውም "ስለርሷ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ አዋቂ አይደለም።" አሉት። "ስለ ምልክቶቿ ይንገሩኝ!" አለ። እሳቸውም "ባሪያ ጌታዋን ልትወልድ ነው ፤ ያልተጫማ፣ የታረዘ፣ ድሃና የፍየል እረኛ የሆኑ ሰዎች ለህንፃዎች ሲሽቀዳደሙ ማየትህ ነው።" አሉት። ዑመር እንዲህ አለ "ከዚያም ሄደ። የተወሰነ ጊዜ ቆየሁ። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ዑመር ሆይ! ጠያቂው ማን እንደነበር አውቀሀልን?" አሉኝ። እኔም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። እሳቸውም "እርሱ ጂብሪል ነው እምነታችሁን ሊያሳውቃችሁ መጥቷችሁ ነው።" አሉ።
بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ذَاتَ يَوْمٍ إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ، حَتَّى جَلَسَ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ، وَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ، أَخْبِرْنِي عَنِ الْإِسْلَامِ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا» قَالَ: صَدَقْتَ، قَالَ: فَعَجِبْنَا لَهُ، يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ، قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ الْإِيمَانِ، قَالَ: «أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ» قَالَ: صَدَقْتَ، قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ الْإِحْسَانِ، قَالَ: «أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ» قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ السَّاعَةِ، قَالَ: «مَا الْمَسْؤُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنَ السَّائِلِ» قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَتِهَا، قَالَ: «أَنْ تَلِدَ الْأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ» قَالَ: ثُمَّ انْطَلَقَ، فَلَبِثْتُ مَلِيًّا ثُمَّ قَالَ لِي: «يَا عُمَرُ، أَتَدْرِي مَنِ السَّائِلُ؟» قُلْتُ: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ، قَالَ: «فَإِنَّهُ جِبْرِيلُ، أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ».
ዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከዕለታት አንድ ቀን ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በሶሐቦች መካከል አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በማይታወቅ ሰው ተመስሎ እንደመጣ ይናገራሉ። ከዚህም ሰውዬ ባህሪዎች መካከል ልብሱ እጅግ የነጣና ፀጉሩም እጅግ የጠቆረ ነበር። በሱ ላይም ድካም፣ አቧራ፣ የፀጉር መንጨባረርና የልብስ መቆሸሽ የመሰሉ የጉዞ ምልክት አይታይበትም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ተቀምጠው ከነበሩ ታዳሚዎች መካከልም አንድም ሰው አላወቀውም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፊት እንደተማሪ አቀማመጥ ተቀመጠ። ስለ ኢስላምም ጠየቃቸው። እሳቸውም እስልምና ማለት ሁለቱን የምስክር ቃላት ማረጋገጥ፣ አምስቱ ሶላቶች ላይ መጠባበቅ፣ ለሚገባው ሰው ዘካ መስጠት፣ ረመዷንን ወር መፆም፣ የቻለ ሰው ግዴታ የሆነውን ሐጅ መፈፀም እንደሆነ ማዕዘናቶቹን በመጥቀስ መለሱለት። ጠያቂውም "እውነት አልክ!" አለ። ሶሐቦችም ከላይ ሲታይ አጠያየቁ አለማወቁን የሚጠቁም፤ ከዛ ደግሞ ትክክለኛ መልስ እንደተመለሰለት ማረጋገጡን በማስተዋላቸው ግራ ተጋቡ። ከዚያም ስለ ኢማን ጠየቃቸው። እሳቸውም እነዚህን ስድስት ማዕዘናት ማመንን የሰበሰበ መልስ መለሱለት። እነሱም:-አላህ በመኖሩ፣ በባህሪያቶቹ፣ መፍጠርን በመሰሉ ድርጊቶቹና በአምልኮም ብቸኛ መሆኑን ማመን፤ አላህ ከብርሃን የፈጠራቸው መላእክቶች የተከበሩ ባሮቹ መሆናቸውን፣ አላህን የማያምፁና በትእዛዙ የሚተገብሩ መሆናቸውን ማመን፤ እንደ ቁርኣን፣ ተውራት፣ ኢንጂልና ሌሎችም ከአላህ ዘንድ በመልክተኞች ላይ በወረዱ መጽሐፍት ማመን፤ የአላህን ሃይማኖት የሚያደርሱ በሆኑ መልክተኞች ማመን ከነሱም መካከል ኑሕ፣ ኢብራሂም፣ ሙሳ፣ ዒሳና የመጨረሻቸው የሆኑት ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂም ወሰለምና ሌሎችም ነቢያቶችና መልክተኞች ይጠቀሳሉ። በመጨረሻው ቀን ማመን፤ እዚህ ውስጥም ከሞት በኋላ ያሉ በቀብርና በበርዘኽ ህይወት እንዲሁም የሰው ልጅ ከሞት በኋላ የሚቀሰቀስና የሚተሳሰብ መመለሻውም ወይ ወደ ጀነት ወይ ወደ እሳት መሆኑን ማመንንም ያካትታል። አላህ በቀደመ ዕውቀቱ መሰረት፣ ጥበቡ ባስፈረደው መልኩ በፍላጎቱ መሰረት ነገሮችን እንደወሰነና በጽሑፍም እንዳሰፈረ ማመን፤ ምድር ላይ የሚከሰቱትም በወሰናትና በፈጠራት ልክ መሆኑንም ማመን ነው። ከዚያም ስለ ኢሕሳን (ስራን ማሳመር) ጠየቃቸው። ኢሕሳን ማለት ልክ አላህን እያዩ እንደሆነ እያሰቡ አላህን መገዛት ነው። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ባይረጋገጥለት (ባይችል) እንኳ ልክ አላህ እርሱን እያየው እንደሆነ በማሰብ አላህን መገዛት ነው። የመጀመሪያው: የ "ሙሻሀዳህ" (አሏህን እያየህ እንደሆነ እያሰብክ የምታመልክበት) ደረጃ ነው እሱም የላቀ ደረጃ ነው። ሁለተኛው ደግሞ የ "ሙራቀባህ" (አሏህ እያየኝ ነው በሚል ሃሳብ የምታመልክበት) ደረጃ ነው። ከዚያም ሰዓቲቱ መቼ እንደሆነች ጠየቃቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰዓቲቱ መከሰቻ ጊዜ አላህ በእውቀቱ ብቸኛ ከሆነበት ጉዳይ አንዱ በመሆኑ ተጠያቂውም ይሁን ጠያቂው ከፍጥረቱ መካከልም አንድም እንደማያውቀው ገለፁ። ከዚያም ስለ ሰዓቲቱ ምልክቶች ጠየቃቸው። ከምልክቶቿ መካከል የጭን ገረዶችና ልጆቻቸው እንደሚበዙ ወይም የልጆች የእናቶቻቸውን ሐቅ አለመወጣታቸው እንደሚበዛ ይህም ከእናቶቻቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር ልክ ከባሪያ ጋር እንዳላቸው አይነት መስተጋብር እንደሚሆን፤ ለበግ እረኞችና ለድሆች በመጨረሻው ዘመን ዱንያ ተዘርግታላቸው በህንፃ ውበትና አሰራር እንደሚፎካከሩ ገለፁ። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠያቂው ጂብሪል እንደነበረና የመጣውም ይህንኑ ቀጥተኛ እምነት ለሶሐቦች ሊያስተምር እንደሆነ ተናገሩ።
...:
የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነ ምግባር ያማረ እንደሆነ፤ ከባልደረቦቻቸው ጋር የሚቀመጡ መሆናቸውንና እነሱም ከሳቸው ጋር እንደሚቀመጡ እንረዳለን።
ለጠያቂ ገር መሆንና ጠያቂን ማቅረብ የተደነገገ መሆኑን፤ ይህም ሳይጨናነቅና ሳይፈራ ለመጠየቅ እንዲመቻች ነው።
ልክ ጂብሪል እውቀት ሊቀስም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፊት ስርአት ያለውን አቀማመጥ በመቀመጥ እንደተገበረ ከአስተማሪ ጋር አደብ መያዝ እንደሚገባ እንረዳለን።
የኢስላም ማዕዘናት አምስት የኢማን መሰረቶች ደግሞ ስድስት መሆናቸውን እንረዳለን።
"ኢስላም" የሚለው ቃልና "ኢማን" የሚለው ቃል አንድ ላይ ሲመጡ "ኢስላም" ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ሲተረጎም "ኢማን" ደግሞ ውስጣዊ በሆኑ ነገሮች ይተረጎማል።
የኢስላም ሃይማኖት የሚበላለጡ ደረጃዎች እንዳሉት መገለፁ፤ የመጀመሪያው ደረጃ: ኢስላም ፣ ሁለተኛው: ኢማን ፣ ሶስተኛው: ኢሕሳን ነው። እርሱ (ኢሕሳን) ከፍተኛው ደረጃ ነው።
የጠያቂ መሰረቱ አለማወቅ ነው። አለማወቅ ነው ለጥያቄ የሚያነሳሳው። ለዚህም ነው ሶሐቦች እየጠየቀም የመልሱን እውነተኝነት ሲያረጋግጥ የተደነቁት።
እሳቸው ኢስላምን ሲያብራሩ በሁለቱ የምስክርነት ቃላት፣ ኢማንን ሲያብራሩም በአላህ ከማመን ነውና የጀመሩት እውቀት ሲሰጥ እጅግ አንገብጋቢ ከሆነ ነጥብ መጀመር እንደሚገባ እንረዳለን።
ጠያቂው የሚያውቀውን ነገር ሌሎችን ለማሳወቅ ሲል የእውቀት ባለቤቶችን መጠየቅ እንደሚችል እንረዳለን።
የሰዓቲቱ እለት እውቀት አላህ በእውቀቱ ከተነጠለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው።
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 36) (8).
ተጨማሪ (9)
التحفة الربانية في شرح الأربعين حديثا النووية (ص7).
شرح الأربعين النووية.
لابن عثيمين (ص19).
فتح القوي المتين في شرح الأربعين وتتمة الخمسين.
للعباد (ص15).
الأحاديث الأربعون النووية وعليها الشرح الموجز المفيد.
لعبد الله المحسن (ص7).
تاج العروس من جواهر القاموس.
للزبيدي (2/ 460).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
48 መጻሕፍትተጨማሪ (48)
- الإسلام أصوله ومبادئه(الإسلام أن تشهد أن لا إله إلا الله، وأن محمداً رسول الله، وتقيم الصلاة وتؤتي الزكاة، وتصوم رمضان، وتحج البيت إن استطعت إليه سبيلاً) [197]،
- الإسلام دين كامل«هُوَ أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ» [1].
- الخطب المنبريةموسوعة الخطب المنبرية (القسم الأول)«الْإِحْسَانَ: أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- الخطب المنبرية موسوعة الخطب المنبرية (القسم الثاني)«أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»"
- الخطب المنبريةموسوعة الخطب المنبرية (القسم الثالث)«الْإِحْسَانُ أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- العقيدة الصحيحةدروس العقيدة الصحيحة«فَأَخْبِرْنِي عَنِ الْإِيمَانِ، قَالَ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَاليَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»
- العلم الواجب بدون فقه وبدون زيادات1(أَن تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ).
- العلم الواجب بدون فقه وبدون زيادات1(أَن تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِن لَّمْ تَكُن تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ).
- الله -جل جلاله- أنيس المحبين وملاذ القاصدين«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنَّ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- الله -جل جلاله- أنيس المحبين وملاذ القاصدين«أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَاليَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»
- الله -جل جلاله- أنيس المحبين وملاذ القاصدين«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- الله -جل جلاله- أنيس المحبين وملاذ القاصدين«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنَّ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- الله -جل جلاله- أنيس المحبين وملاذ القاصدين«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنَّ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- المناهج التعليمية - الصف السادسالمناهج الدراسية - الفقه - الصف السادس «الإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا»[9].
- المناهج التعليمية - الصف السادسالمناهج الدراسية - الفقه - الصف السادس «الإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا»[24].
- ثلاثة الأصول وأدلتهاقَالَ: أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ.
- ثلاثة الأصول وأدلتهاقَالَ: مَا المَسْؤُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنَ السَّائِلِ.
- حراسة التوحيدالعقيدة الصحيحة وما يضادها «الإِيمَانُ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَاليَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»[1].
- خذ عقيدتك من الكتاب والسنة الصحيحة"الإسلام أن تشهد أن لا إله إِلا الله وأن محمدًا رسول الله، وتُقيم الصلاة، وتؤتي الزَّكاة، وتصوم رمضان، وتَحجَّ البيت إن استطعت إليه سبيلًا".
- خذ عقيدتك من الكتاب والسنة الصحيحة"الإيمان: أن تؤمن باللهِ، وملائكتِه وكتبه، ورسلِه، واليوم الآخر، وتؤمن بالقدَر خيره وشره"
- خذ عقيدتك من الكتاب والسنة الصحيحة«الإحسان أن تعبدَ الله كأنك تراه، فإن لم تكن تراهُ فإنه يَرَاك»
- خطبة عرفة(الإِسْلاَمُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا).
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 1 «بَيْنَمَا نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ رسولِ الله صلى الله عليه وسلم ، ذَاتَ يَوْمٍ إذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَديدُ بَياضِ الثِّيَابِ، شديدُ سَوَادِ الشَّعْرِ، لا يُرَىٰ عَلَيْهِ أَثرُ السَّفَرِ، وَلا يَعْرِفُهُ منَّا أحَدٌ، حَتَّىٰ جَلَسَ إلَ
- سؤال وجواب حول الإسلام«الإِحْسَانُ أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- شرح الأصول الثلاثة«أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ» [21]
- شرح الأصول الثلاثةقَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِيمَانِ؟ قَالَ: «أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ» قَالَ: صَدَقْتَ.
- عقيدة الأئمة الأربعة«أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»
- فضل الإسلام{ الإسلام أن تشهد أن لا إله إلا الله، وأن محمدا رسول الله، وتقيم الصلاة، وتؤتي الزكاة، وتصوم رمضان، وتحج البيت إن استطعت إليه سبيلا } [8].
- قاموس الكبائر موسوعة الكبائر - المجموعة الأولى«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ، فَإِنَّهُ يَرَاكَ» [50].
- قاموس الكبائر«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ، فَإِنَّهُ يَرَاكَ» [50].
- كيف أكون مسلمًا؟1(الإِسْلاَمُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلاَةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا)
- ما لا يسع أطفال المسلمين جهله«فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِيمَانِ، قَالَ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَاليَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»[3].
- مادة العقيدة الإسلامية(أن تؤمن بالله، وملائكته، وكتبه، ورسله، واليوم الآخر، وتؤمن بالقدر خيره وشره).[65]
- مادة العقيدة الإسلامية(قَالَ فأخبرني عَنِ السَّاعَةِ. قَالَ مَا الْمَسْئُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنَ السَّائِلِ. قَالَ فأخبرني عَنْ أَمَارَتِهَا. قَالَ أَنْ تَلِدَ الأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ
- مجموعة زاد التفسير (2)التفسير 2«ما المسْؤُولُ عَنْها بأعْلَمَ من السَّائلِ».
- مجموعة زاد الحديث (1)الحديث 1قَالَ: بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ الله صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ، إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ، حَتَّى جَل
- مشروع المنهج التعليميمادة التوحيد مستوى 2«الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ ﷺ وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا»، قَالَ: صَدَقْتَ، قَالَ: ف
- مشروع منهاج زادكزادك 1 طالببَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ، إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ، حَتَّى جَلَسَ إِ
- موسوعة الإيمانفعن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال: بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ، إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِ
- موسوعة الإيمان«أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ». قَالَ: صَدَقْتَ.
- نبذة في العقيدة الإسلامية (شرح أصول الإيمان)نبذة في العقيدة الإسلامية«الْإِيمَانُ: أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ: خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»[3].
- نبراس طالب (1)1«أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ»، قَالَ: صَدَقْتَ.
- نبراس طالب (1)1«الْإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا».
- نبراس طالب (1)1«أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ».
- نبراس طالب (1)1«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ».
- نبراس طالب (1)1«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- نبراس طالب (2)نبراس طالب (2) «أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»
- نبراس طالب (3)نبراس طالب 3«أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ»