Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 45 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"
ሶሒሕ ነው። ኢማሙ አሕመድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ ኢብኑ ሒባን በሶሒሓቸው እና ሓኪም ዘግበውታል
«" በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።»
ሶሒሕ ነው። የመጀመሪያው ሐዲሥ፡ ሙስሊም ዘግበውታል፣ ሁለተኛው ሐዲሥ ደግሞ፡ አሕመድ እና ዳሪሚይ ዘግበውታል
«ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወደ የመን ላኩት። በየመን ውስጥ ይሰራ ስለነበር መጠጥም ጠየቃቸው። እርሳቸውም "ምንድናት?" አሉት። እርሱም: "ቢትዕ እና ሚዝር ናቸው።" አላቸው። (ሐዲሡን እያስተላለፈ ላለው) ለአቡ ቡርዳ "ቢትዕ ምንድን ነው?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም "በማር የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ነው።" አላቸው። "ሚዝርስ?" ብለው ሲጠይቁት "በገብስ የሚሰራ አስካሪ መጠጥ ነው።" ብሎ መለሰላቸው። ነቢዩም "ሁሉም አስካሪ ነገር ሐራም ነው።" ብለው መለሱለት።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
"ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"»
ሶሒሕ ነው። ኢማሙ አሕመድ፣ ቲርሚዚይ፣ ኢብኑ ማጃህ እና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል
"አራት (ባሕርያት) በእርሱ ላይ ያለበት ሰው ሙናፊቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ባህሪዎች ውስጥ አንዱ ያለበት ደግሞ እስኪተዋት ድረስ አንድ የሙናፊቅነት ባህሪ ይኖረዋል፦ ሲናገር ይዋሻል፤ ቀጠሮ የያዘ ጊዜ ያፈርሳል፤ ሲከራከር ወሰን ያልፋል፤ ቃልኪዳን ከገባ በኋላ ቃልኪዳኑን ይክዳል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
"ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ጋር ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመና ቢደርሱና ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን ሊሞላ በቀረበ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣ ከዚያም በኔ አንድንም ሳታጋራብኝ ብትገናኘኝ እኔም ምድርን ሊሞላ በቀረበ ምህረት ወዳንተ እመጣለሁ።›"»
ሐሰን ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ይዞት የመጣው አዲስ ፈሊጥ ውድቅ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል