Skip to content

"አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል።

ከሙዓዊያህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦

"አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል። እኔ አከፋፋይ ብቻ ነኝ አላህ ነው የሚሰጠው። ይህች ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ የቆመች ከመሆን አትወገድም! የአላህ ትእዛዝ እስክትመጣ ድረስም የተቃረናቸው ሁሉ አይጎዳቸውም።"

«مَنْ يُرِدِ اللهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ، وَإِنَّمَا أَنَا قَاسِمٌ، وَاللهُ يُعْطِي، وَلَنْ تَزَالَ هَذِهِ الْأُمَّةُ قَائِمَةً عَلَى أَمْرِ اللهِ، لَا يَضُرُّهُمْ مَنْ خَالَفَهُمْ، حَتَّى يَأْتِيَ أَمْرُ اللهِ».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ሃይማኖቱን መገንዘብ እንደሚቸረው፤ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ከሰጣቸው ሲሳይ፣ ዕውቀትና ሌሎችም ነገሮች የሚያከፋፍሉና የሚያሰራጩ አከፋፋይ ብቻ እንጂ ትክክለኛው ሰጪ አላህ ብቻ እንደሆነ ከሱ ውጪ ያሉት ከሰበብነት የዘለለ ከርሱ ፈቃድ ውጪ እንደማይጠቅሙ፤ ይህ ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ ከመቆም እንደማይወገድና ትንሳኤ እስከሚቆም ድረስም የተፃረራቸው እንደማይጎዳቸው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

የቃላት ፍቺ

.....:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ሸሪዐዊ ዕውቀት እና እርሱን መማር ያለው ትሩፋት ትልቅ መሆኑንና በርሱም ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል።

በእዚህ ኡማህ ውስጥ በእውነት ላይ የሚቆም መኖሩ የማይቀር ጉዳይ መሆኑንና ከእውነተኛ መንገድ አንዱ ሲገለል ሌላው በእውነት ላይ ይቆማል።

ሃይማኖትን መገንዘብ አላህ ለባሪያው መልካም ከመሻቱ የሚመደብ ነው።

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚሰጡት በአላህ ትእዛዝና ፍላጎት ብቻ መሆኑንና ያለርሱ ፈቃድ አንድም ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ተረድተናል።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 25) (71).

ሶሒሕ ሙስሊም (2/ 718) (1037).

ተጨማሪ (8)

توضيح الأحكام من بلوغ المرام.

للبسام (7/ 485).

منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (10/ 324).

فتح ذي الجلال والإكرام.

لابن عثيمين (6/ 424).

سبل السلام بشرح بلوغ المرام.

للصنعاني (2/ 688).