"ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"»
ከበራእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"»
«مَا مِنْ مُسْلِمَيْنِ يَلْتَقِيَانِ فَيَتَصَافَحَانِ إِلَّا غُفِرَ لَهُمَا قَبْلَ أَنْ يَفْتَرِقَا».
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሁለት ሙስሊሞች በመንገድና መሰል ቦታ ተገናኝተው አንዱ ሌላኛውን በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተሰጣጡ ለነርሱ (ከቦታው) በአካል ወይም ከመጨባበጡ እጃቸውን ከማለያየታቸው በፊት ወንጀላቸው ይማራል ብለው ተናገሩ።
በመገናኘት ወቅት መጨባበጥ እንደሚወደድና በዚህም ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
መናዊይ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሱና ሌላ ችግር እስከሌለ ድረስ ቀኝ እጅን ቀኝ እጅ ላይ በማሳረፍ ካልሆነ በቀር አይገኝም።»
ሰላምታን በማብዛት ላይ መነሳሳቱንና አንድ ሙስሊም ሌላውን ሙስሊም ወንድሙ በመጨበጥ የሚያገኘው ምንዳ ትልቅነት መገለፁን እንረዳለን።
አጅነቢይ (ባዳ የሆነችን) ሴት መጨበጥ የመሰለው ክልክል የሆነ መጨባበጥ ከዚህ ሐዲሥ ውጭ ነው።
ሱነን አቡዳውድ (7/ 502) (5212).
ሱነን ቲርሚዚ (4/ 447) (2727).
ሱነን ኢብኑ ማጀህ (4/ 654) (3703).
ሙስነድ አሕመድ (30/ 517) (18547).
ተጨማሪ (4)
بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.
لسليم الهلالي (2/ 152).
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (1/ 680).