Skip to content

እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ)

ከአቡ ዓብደላህ ጃቢር ቢን ዐብደላህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው:

«አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ) በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - “አዎን!” አሉት።»

أَنَّ رَجُلًا سَأَلَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: أَرَأَيْتَ إِذَا صَلَّيْتُ المَكْتُوبَاتِ، وَصُمْتُ رَمَضَانَ، وَأَحْلَلْتُ الحَلَالَ، وَحَرَّمْتُ الحَرَامَ، وَلَمْ أَزِدْ عَلَى ذَلِكَ شَيْئًا، أَأَدْخُلُ الجَنَّةَ؟ قَالَ: «نَعَمْ».

ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ከዚህም ሱና ፆሞችን ያልጨመረ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

አንድ ሙስሊም መጨረሻው ጀነት መግባት እንዲሆን፥ ግዴታዎችን በመተግበር እና ክልከላን በመተው ላይ ጥረት ሊኖረው ይገባል ።

ሐላል ፍቁድ ነገሮችን ፍቁድነታቸውን በማመን መተግበርና ክልክል ነገሮችን ክልክልነታቸውን በማመን መራቅ አሳሳቢ (ወሳኝ) ጉዳይ መሆኑን ፤

ግዴታዎችን መፈፀምና ክልክሎችን መተው ጀነት መግቢያ (ሰበብ) ምክንያት ነው።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 44) (15).

ተጨማሪ (3)

جامع العلوم والحكم (1/513).

شرح الأربعين النووية للعثيمين (ص: 215).

فتح القوي المتين في شرح الأربعين للعباد (ص 77).