Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 91 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ

ዘጋቢ

ሁሉንም ዘጋቢዎች አሳይ (49)
'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች። ይህም አንዳቸው ዉዱእ ሲያደርግ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከሶላት በስተቀር ሳያንቀሳቅሰው ከሶላትም በስተቀር ሌላን ሳይፈልግ ወደ መስጅድ ከመጣ መስጂድ እስኪገባ ድረስ በሚራመደው እያንዳንዱ እርምጃ ልክ ለርሱ ደረጃው ከፍ ይደረግለታል፤ ወንጀሉም ከርሱ ላይ በሷው ይራገፍለታል። መስጂድ የገባ ገዜም በሶላቷ ምክንያት እስከተጠመደ ድረስ ሶላት ውስጥ ነው። አንዳችሁ በሰገደበት ስፍራ ላይ እስከዘወተረ ድረስም ሰዎችን እስካላወከና ዉዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላእክቶች በርሱ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ። 'አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው' ይላሉም።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። እኔም የአላህ መልክተኛ ሆይ! እናትና አባቴ ፊዳ ይሁንሎና በተክቢራ እና በፋቲሓ መካከል ዝምታዎን አይቻለሁና ምንድን ነው የሚሉት? አልኳቸው። እርሳቸውም " 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ አልላሁምመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዱ ሚነድደነስ፣ አልላሁምመ ኢግሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ' ነው የምለው" አሉኝ። (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ መካከል እንዳራራቅከው በኔና በወንጀሌ መካከል አራርቅ! አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፉ እንደሚጠራው እኔንም ከወንጀሎቼ አጥራኝ! አላህ ሆይ በጤዛ፣ በውሃና በበረዶ ከወንጀሎቼ እጠበኝ። ማለት ነው።)»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።