Skip to content

ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።"

ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦

"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ ዘመን በምፅዋት፣ ነፃ በማውጣትና ዝምድና በመቀጠል የምፈፅማቸው አምልኮዎች ነበሩ በእነሱ እመነዳለውን?" አልኳቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለው መለሱለት፦ "ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።"

قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَرَأَيْتَ أَشْيَاءَ كُنْتُ أَتَحَنَّثُ بِهَا فِي الجَاهِلِيَّةِ مِنْ صَدَقَةٍ أَوْ عَتَاقَةٍ، وَصِلَةِ رَحِمٍ، فَهَلْ فِيهَا مِنْ أَجْرٍ؟ فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَسْلَمْتَ عَلَى مَا سَلَفَ مِنْ خَيْرٍ».

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ካፊር የሰለመ ጊዜ ከመስለሙ በፊት በጃሂሊያ ዘመን ይሠራቸው በነበሩት እንደ ሰደቃ፣ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ዝምድና መቀጠል የመሰሉ መልካም ሥራዎች እንደሚመነዳ አብራሩ።

የቃላት ፍቺ

أتحنث: أتعبد.

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ካፊር በዱንያ ለሠራቸው መልካም ሥራዎች በዛው ክህደት ላይ ከሞተ በአኺራ አይመነዳበትም።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (2/ 114) (1436).

ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 113) (123).

ተጨማሪ (5)

المفهم (1/332).

شرح النووي على مسلم (2/140).

عمدة القاري شرح صحيح البخاري (22/ 96).

فتح الباري لابن حجر (3/ 302).

البحر المحيط الثجاج (3/499).