Skip to content
የሱራዎች ዝርዝር /

الإسرَاء

الإسرَاء is chapter 17 of the Quran and has 111 verses. This page presents it in full in the Uthmani script, with a verse-by-verse translation of its meaning.

111 አንቀጾች የሱራ ቁጥር 17
ወደ አንቀጽ ይሂዱ
አማርኛ · Zain
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِيٓ أَسۡرَىٰ بِعَبۡدِهِۦ لَيۡلٗا مِّنَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ إِلَى ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡأَقۡصَا ٱلَّذِي بَٰرَكۡنَا حَوۡلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنۡ ءَايَٰتِنَآۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ

ጥራት ለዚያ ባሪያውን (ሙሐመድን) ከተከበረው የሐረም መስጊድ ወደ እዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ሩቁ (አል አቅሷ) መስጊድ በሌሊት ለወሰደው አምላክ ለአላህ ይሁን:: ይህን ያደረግን ተዓምራታችንን ልናሳየው ነው:: እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚዉና ተመልካቹ ነው::

وَءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَجَعَلۡنَٰهُ هُدٗى لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُواْ مِن دُونِي وَكِيلٗا

ለሙሳም (ተውራት የተባለውን) መጽሐፍ ሰጠነውና ለኢስራኢል ልጆች መሪ አደረግነው:: ከእኔ ሌላ ወኪል (መጠጊያ) አድርጋችሁ ማንንም አታድርጉ“ስንልም አዘዝናቸው::

ذُرِّيَّةَ مَنۡ حَمَلۡنَا مَعَ نُوحٍۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَبۡدٗا شَكُورٗا

«ከኑህ ጋር (በመርከቧ ላይ) የጫንናቸው (አማኝ )ዝርዮች ሆይ! (አላህን ተገዙ)፤ ኑህ በእርግጥ አምላኩን በብዛት አመስጋኝ ባሪያ ነበርና» አልናቸው።

وَقَضَيۡنَآ إِلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ لَتُفۡسِدُنَّ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَّتَيۡنِ وَلَتَعۡلُنَّ عُلُوّٗا كَبِيرٗا

ለኢስራኢል ልጆችም፡ “በምድር ላይ ሁለት ጊዜ ጥፋት ትፈጽማላችሁ:: አለቅጥም አምባገነን ትሆናላችሁ::” ስንል በመጽሐፉ ውስጥ ገለጽን::

فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ أُولَىٰهُمَا بَعَثۡنَا عَلَيۡكُمۡ عِبَادٗا لَّنَآ أُوْلِي بَأۡسٖ شَدِيدٖ فَجَاسُواْ خِلَٰلَ ٱلدِّيَارِۚ وَكَانَ وَعۡدٗا مَّفۡعُولٗا

ከሁለቱ የመጀመሪያው ጥፋት መፈጸሚያ ወቅቱ በደረሰ ጊዜ የበረታ ኃይል ያላቸውን ባሮቻችንን በእናነተ ላይ ላክንባችሁ:: እነርሱም ቤቶችን ሁሉ በረበሩ:: ይህ መፈጸሙ የማይቀር ውሳኔ ነበር::