Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 2 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«በአቡ ጦልሓ ቤት ውስጥ ለሰዎች መጠጥ እየቀዳሁ የማጠጣው እኔ ነበርኩ። የዛን ግዜ ይጠጡት የነበረው አስካሪ መጠጥ በተምር የሚሰራ ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ተብሎ አዋጅ እንዲነገር አዘዙ: "አዋጅ! በርግጥ አስካሪ መጠጥ ክልክል ተደርጓል።" አቡ ጦልሓ ለኔ እንዲህ አለኝ: "ውጣና ድፋው" እኔም ወጥቼ ደፋሁት በመዲናም መንገድ ፈሰሰ። አንዳንድ ሰዎችም "ሰዎች አስካሪ መጠጥ በሆዳቸው እያለ አለቀላቸዋ!" አሉ። እነርሱን በማስመልከትም አላህ ይህንን አወረደ: {በእነዚያ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ (ከመከልከሉ በፊት) በተመገቡት ነገር ኀጢአት የለባቸውም።… } [አልማኢዳህ: 93]»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
{በእርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ) በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።} [አልሐጅ: 25] በሚለው የአላህ ንግግር ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰውዬ ዓደን አብየን ላይ ሆኖ እንኳ ሐረም ውስጥ በደል ለመስራት ቢያስብ አላህ አሳማሚ ቅጣትን ያቀምሰዋል።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ እና አል-ሓኪም ዘግበውታል