Skip to content

«ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

«ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ። "ሁለቱም አያፀዱም።" ብለዋል።»

إِنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نَهَى أَنْ يُسْتَنْجَى بِرَوْثٍ أَوْ عَظْمٍ، وَقَالَ: «إِنَّهُمَا لَا تُطَهِّرَانِ».

ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከሸና ወይም ሰገራውን ከተጠቀመ በኋላ በእንስሶች አጥንት ወይም በፍጋቸውና በፋንዲያቸው ከማደራረቅ ከለከሉ። እንዲህም አሉ: እርሷ ነጃሳን አታስወግድምም አታፀዳምም።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

አንዳንድ የመፀዳዳትና የኢስቲንጃእ ስነስርዓት መገለፁ።

በፋንዲያ (ፍግ) ኢስቲጅማር ማድረግ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ወይ ነጃሳ ስለሆነ ነው ወይም የጂን እንስሶች ቀለብ ስለሆነ ነው።

በአጥንት ኢስቲጅማር ማድረግ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ወይ ነጂስ ነው። ወይም ለጂኖች ምግብ ስለሆነ ነው።

ማጣቀሻዎች

ሱነን ዳረቁጥኒይ (1/ 88) (152).

ተጨማሪ (6)

توضيح الأحكام مِن بلوغ المرام.

لعبد الله البسام (1/ 355).

سبل السلام.

للصنعاني (1/ 118).

مرقاة المفاتيح شرح مشكاة المصابيح.

لعلي القاري (1/ 374).