Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 8 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ" አቡ አዩብ እንዲህ አለ "ሻም ስንገባ ወደ ቂብላ አቅጣጫ የተገነባ መፀዳጃ ቤት አገኘን። ትንሽ ዘንበል እያልን እየተፀዳዳን አላህንም ምህረት እንጠይቀዋለን።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመፀዳጃ ቤት የወጡ ጊዜ "ጉፍራነክ" ይሉ ነበር።» (ትርጉሙም "ምህረትህን እለምንሃለሁ" ማለት ነው።)
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት ይገቡና እኔና የኔ እኩያ የሆነ ልጅም ውሃ የያዘ ዕቃና አንካሴ ተሸክመን እንወስድላቸው ነበር። በውሃውም እስቲንጃእ ያደርጉበት ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ። "ሁለቱም አያፀዱም።" ብለዋል።»
ሶሒሕ ነው። ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።
«አጋርያኖች ለኛ እንዲህ አሉን: "እኔ እንደማየው ባልደረባችሁ እንዴት እንደምትፀዳዱ ሳይቀር ያስተምራችኋል አይደል?" እኔም እንዲህ በማለት መለስኩላቸው አዎ እርሳቸው እያንዳንዳችን በቀኝ እጁ ከመጥራራት (ኢስቲንጃእ ከማድረግ) ወይም ወደ ቂብላ አቅጣጫ ዞሮ ከመፀዳዳት ከልክለውናል። በፍግና በአጥንት ከመፀዳዳት (ኢስቲንጃእ ከማድረግም) ከልክለውናል። እንዲህም ብለውናል "አንዳችሁ ከሶስት ድንጋይ ባነሰ ኢስቲንጃእ እንዳያደርግ (እንዳያጥራራ)።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።