Skip to content

'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ሰሙ፡ "በካዕባ ይሁንብኝ በፍፁም!" ኢብኑ ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዲሁ አሉ፡ "ከአሏህ ውጭ ባለ አካል አይማልም! ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁና

'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"

«مَنْ حَلَفَ بِغَيْرِ اللهِ فَقَدْ كَفَرَ أَوْ أَشْرَكَ».

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአሏህ ወይም በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር ከዛ ውጪ በሆነ መሀላ የማለ ሰው በአላህ ክዷል ወይም አጋርቷል ብለው ተናገሩ። ምክንያቱም በአንድ አካል መማል እሱን ማላቃችንን ያስፈርዳል፤ በእውነቱ ልቅና ደግሞ የሚገባው ለአሏህ ብቻ ነው። ስለዚህም በሱ ወይም ከስምና ባህሪዎቹ መካከል በአንዱ ካልሆነ በስተቀር አይማልም። ይህ መሀላ ከትንሹ ሽርክ የሚመደብ ነው። ይሁን እንጂ የማለው ሰው የማለበትን አካል እንደ አሏህ ወይም ከዛም በላይ አልቆት ከሆነ ግን መሃላው ትልቁ ሽርክ ይሆናል።

የቃላት ፍቺ

من حلف: الحلف: اليمين، وهي توكيد الحكم بذكر معظّم تطمئن له نفس المخاطب.

كفر أو أشرك: يحتمل أن يكون هذا شكًّا من الراوي، ويحتمل أن تكون "أو" بمعنى الواو فيكون كفر وأشرك.

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በመሀላ ማላቅ ጥራት የተገባው የአሏህ ሐቅ ነው። በመሆኑም በአላህ ፣ በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማልም።

ሰሓቦች በመልካም ለማዘዝ እና ከመጥፎ ለመከልከል የነበራቸውን ጉጉት ያሳያል፤ በተለይም ጥፋቱ ሽርክን ወይም ክህደትን የሚመለከት ሲሆን የበለጠ ጉጉት አላቸው።

ማጣቀሻዎች

ሱነን ቲርሚዚ (3/ 194) (1535).

ሱነን አቡዳውድ (5/ 154- 155) (3251).

ሙስነድ አሕመድ (9/ 249) (5346).

(9/ 275) (5375).

(10/ 249) (6072).

(1/ 343).

ተጨማሪ (11)

فتح المجيد شرح كتاب التوحيد.

لعبد الرحمن التميمي (ص413).

القول المفيد على كتاب التوحيد.

لابن عثيمين (2/ 214).

الملخص في شرح كتاب التوحيد.

لصالح الفوزان (ص326).

الجديد في شرح كتاب التوحيد.

لمحمد القرعاوي (ص365).

التمهيد لشرح كتاب التوحيد.

لصالح آل الشيخ (ص452).

فتاوى اللجنة الدائمة.