Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 3 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ‐ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ‐ ከስለት ከለከሉ። እንዲህም አሉ "እርሱ መልካምን ይዞ አይመጣም። በስለት የሚገኘው ትርፍ ስስታም ተገዶ ማውጣቱ ብቻ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የሙስሊምን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ እየዋሸ የማለ ሰው አላህ በርሱ ላይ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል።" አሽዓሥም እንዲህ አለ: "በአላህ እምላለሁ! ይህንን የተናገሩት በኔ ምክንያት ነበር። በኔና በአንድ አይሁድ መካከል የመሬት ውል ነበረንና ካደኝ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድም ለፍርድ አቆምኩት። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ማስረጃ አለህን?" አሉኝ። እኔም "የለኝም።" አልኩኝ። ከዛም ለአይሁዱ "ማል።" አሉት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዲህ ከሆነማ ምሎ ገንዘቤን ይወስዳል።" አልኳቸው። አላህም {እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ ... } ሙሉ አንቀፁን አወረደ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ከተወሰኑ የአሽዐር ተወላጆች ጋር በመሆን ለጂሀድ መጓጓዣ እንዲሰጡን ለመጠየቅ መጣሁ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "እኔ ዘንድ የምሰጣችሁ መጓጓዣ የለኝምና በአላህ እምላለሁ! መጓጓዣ አልሰጣችሁም።" ከዚያም አላህ የሻው ወቅት ያህል ቆየን። ግመል መጣላቸውና ለኛም ሶስት ግመል እንዲሰጠን አዘዙ። ግመሉን ይዘን ጉዞ የወጣን ጊዜ አንዳችን ለአንዳችን "አላህ በዚህ ግመል አይባርክልንና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ የጂሀድ መጓጓዣ ግመል ፈልገን መጣን። እርሳቸውም መጓጓዣ እንደማይሰጡን ማሉና ቀጥሎ ሰጡን! (ለመሀላቸው ብለን መቀበል አልነበረብንም።)" ተባባልን።» አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት ይህንን አወሳንላቸው። እርሳቸውም "እኔ አይደለሁም መጓጓዣ የሰጠዋችሁ አላህ ነው የሰጣችሁ። እኔ ወላሂ አላህ ከሻ በአንድ ጉዳይ ከማልኩ በኋላ ተቃራኒው የተሻለ ሆኖ ከታየኝ የተሻለውን ፈፅሜ ለመሀላዬ ማካካሻ አደርጋለሁ እንጂ ከዚህ ውጪ ሌላ አላደርግም።" አሉን።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።