Skip to content
የሱራዎች ዝርዝር /

الشُّورى

الشُّورى is chapter 42 of the Quran and has 53 verses. This page presents it in full in the Uthmani script, with a verse-by-verse translation of its meaning.

53 አንቀጾች የሱራ ቁጥር 42
ወደ አንቀጽ ይሂዱ
አማርኛ · Sadiq
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

عٓسٓقٓ

ዓይን ሲን ቃፍ፤

كَذَٰلِكَ يُوحِيٓ إِلَيۡكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكَ ٱللَّهُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

እንደዚሁ (በዚህች ሱራ ውስጥ እንዳለው) አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ወዳንተ ያወርዳል፡፡ ወደ እነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች (አውርዷል)፡፡

لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡعَظِيمُ

በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው፡፡

تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرۡنَ مِن فَوۡقِهِنَّۚ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يُسَبِّحُونَ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡ وَيَسۡتَغۡفِرُونَ لِمَن فِي ٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ

(ከአላህ ፍራቻ) ሰማያት ከበላያቸው ሊቀደዱ ይቀርባሉ፡፡ መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፡፡ በምድርም ላለው ፍጡር ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ ንቁ! አላህ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነው፡፡