Skip to content
የሱራዎች ዝርዝር /

مَريَم

مَريَم is chapter 19 of the Quran and has 98 verses. This page presents it in full in the Uthmani script, with a verse-by-verse translation of its meaning.

98 አንቀጾች የሱራ ቁጥር 19
ወደ አንቀጽ ይሂዱ
አማርኛ · Zain
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

كٓهيعٓصٓ

ካፍ፤ ሃ፤ ያ፤ ዐይን፤ ሷድ፤

ذِكۡرُ رَحۡمَتِ رَبِّكَ عَبۡدَهُۥ زَكَرِيَّآ

ይህ ጌታህ ባርያውን ዘከሪያን በችሮታው ያወሳበት ነው::

إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ نِدَآءً خَفِيّٗا

ጌታውን የሚስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ::

قَالَ رَبِّ إِنِّي وَهَنَ ٱلۡعَظۡمُ مِنِّي وَٱشۡتَعَلَ ٱلرَّأۡسُ شَيۡبٗا وَلَمۡ أَكُنۢ بِدُعَآئِكَ رَبِّ شَقِيّٗا

(እንዲህም) አለ: «ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴም ደከመ:: ራሴም በሽበት ተንቀለቀለ። ጌታዬ ሆይ! አንተንም በመለመኔ፤ ምንጊዜም ዕድለ ቢስ እልሆንኩም።

وَإِنِّي خِفۡتُ ٱلۡمَوَٰلِيَ مِن وَرَآءِي وَكَانَتِ ٱمۡرَأَتِي عَاقِرٗا فَهَبۡ لِي مِن لَّدُنكَ وَلِيّٗا

«እኔም ከበኋላዬ (ከሞትኩ በኋላ) ዘመዶቼን (ከእምነት እንዳይወጡ) ፈራሁ:: ሚስቴም መካን ነበረች:: ስለዚህ ካንተ ዘንድ ለእኔ ልጅን ስጠኝ::