Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 14 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። እኔም የአላህ መልክተኛ ሆይ! እናትና አባቴ ፊዳ ይሁንሎና በተክቢራ እና በፋቲሓ መካከል ዝምታዎን አይቻለሁና ምንድን ነው የሚሉት? አልኳቸው። እርሳቸውም " 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ አልላሁምመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዱ ሚነድደነስ፣ አልላሁምመ ኢግሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ' ነው የምለው" አሉኝ። (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ መካከል እንዳራራቅከው በኔና በወንጀሌ መካከል አራርቅ! አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፉ እንደሚጠራው እኔንም ከወንጀሎቼ አጥራኝ! አላህ ሆይ በጤዛ፣ በውሃና በበረዶ ከወንጀሎቼ እጠበኝ። ማለት ነው።)»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው ጀነት ለመግባት ከሞት በቀር ምንም አይከለክለውም።"»
ሶሒሕ ነው። ነሳኢ በኩብራ ዘግቦታል።
የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሩኩዕ ወገባቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜ "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ አላሁመ ረበና ለከል ሐምዱ ሚልአስ-ሰማዋቲ ወልአርድ ወሚልአ ማ ሺእተ ሚን ሸይኢን በዕዱ" ይሉ ነበር። ትርጉሙም "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው። አላህ ሆይ! ሰማያትን የሞላ፣ ምድርን የሞላ፣ ከነዚህም በኋላ ያሉ የፈለግከውን ነገሮችን የሞላ ምስጋና ላንተ የተገባ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«ከሁሉም (ግዴታ) ሶላት በኋላ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሓነሏህ) ያለ፤ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ (አልሐምዱ ሊላህ) ያለ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ያለ፤ ይህም በድምሩ ዘጠና ዘጠኝ ሲሆን መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ወንጀሉ የባህር አረፋ አምሳያ ቢደርስ እንኳ ይማራል።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ኢብኑ ዙበይር በሁሉም ሶላት ካሰላመተ በኃላ እንዲህ ይሉ ነበር። 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ፤ ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ፤ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወላነዕቡዱ ኢላ ኢያህ ለሁ አንኒዕመህ ወለሁልፈድል ወለሁ አሥሠናኡል ሐሰን፤ ላኢላሃ ኢለሏሁ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲነ ወለው ከሪሃል ካፊሩን' አስከትለውም እንዲህ አሉ ' የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሁሉም ሶላቶች በኋላ እነዚህን ውዳሴዎች ይሉ ነበር።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ: "ሙዓዝ ሆይ! ወላሂ እኔ እወድሃለሁ።" እንዲህም አሉ "ሙዓዝ ሆይ! ከየሁሉም ሶላት መጠናቀቂያ ላይ 'አልላሁመ አዒንኒ ዓላ ዚክሪከ፣ ወሹክሪከ፣ ወሑስኒ ዒባደቲክ' ማለትን እንዳትተው አደራ እልሃለሁ።" አሉኝ።» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመር ላይ አግዘኝ።) ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ እና አሕመድ ዘግበውታል
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ይሉ ነበር።» ትርጉሙም "ጌታችን ሆይ! ከምስጋና ጋር ጥራት የተገባህ ነህ! አላህ ሆይ! ማረኝ።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።