Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 8 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ማነብነብ (ሩቃ) ፣ ሂርዝ ማንጠልጠልና መስተፋቅር ሽርክ ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ከዑክል ወይም ከዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ መጡ። መዲና ስላልተስማማቸው ሆዳቸውን ታመሙ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወተት ወዳላቸው ግመሎች በመሄድ ከሽንታቸውና ከወተታቸው እንዲጠጡ አዘዟቸው። የተሻላቸውም ጊዜ የነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እረኛ ገድለው ግመሎቹን እየነዱ ሄዱ። የመግደላቸው ወሬም የቀኑ መጀመሪያ ላይ ደረሰ። ፈለጋቸውን አስተከትለውም ሰዎችን ላኩ። ቀኑ ረፈድ ያለ ጊዜም ተይዘው መጡ። በነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ መሰረትም እጃቸውና እግራቸው ተቆረጠ። አይኖቻቸውም ተተኮሰ። ተኳሳ ድንጋይ ላይም ተጣሉ። ውሃን ይጠይቃሉ ግን ማንም አይሰጣቸውም ነበር። አቡ ቂላባ እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሰዎች ሰረቁ፤ ገደሉ፤ ከእምነት በኋላም ካዱ፤ አላህና መልክተኛውንም ተዋጉ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ መጣና እንዲህ አላቸው: "ሙሐመድ ሆይ! አመመህ እንዴ?" እርሳቸውም "አዎ" አሉ። እርሱም: "ቢስሚላሂ አርቂክ ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚክ ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዐይኒን ሓሲዲን አላሁ የሽፊክ ቢስሚላሂ አርቂክ" (ትርጉሙም: በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ከሁሉም ከሚያውክህ ነገር ፣ ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን አላህ እንዲፈውስህ በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ።) አላቸው።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«እጅህን የሚያምህ ሰውነት ላይ አድርግና ሶስት ጊዜ "ቢስሚላህ" በል። ሰባት ጊዜ ደግሞ "አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚንሸሪ ማአጂዱ ወኡሓዚሩ" በል።» አሉት።" ትርጉሙም "ከሚሰማኝ ህመምና ከምፈራው አደጋ ክፋት በአላህና በችሎታው እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ህመምተኛ የሄዱ ጊዜ እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉለት ነበር: "አዝሂቢልባስ ረበንናስ ወሽፊ አንተ ሻፊ፤ ላ ሺፋአ ኢላ ሺፋኡክ፣ ሺፋአን ላዩጋዲሩ ሰቀማ"» ትርጉሙም "የሰዎች ጌታ የሆንከው ሆይ! በሽታውን አስወግድ። አንተ ፈዋሽ ነህና ፈውሰው። በሽታን የማያስቀር ከሆነው ከአንተ ፈውስ በቀርም ሌላ ፈውስ የለም።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ እጠይቃለሁ።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ነገ ይህንን ባንዲራ አላህ በርሱ እጅ ድልን ለሚያጎናፅፍ፣ አላህና መልክተኛውን ለሚወድ፣ አላህና መልክተኛውም የሚወዱት ለሆነ ሰው እሰጠዋለሁ።" ሰዎችም ለማን ነው የሚሰጠው? በሚል ሌሊታቸውን ተጠምደውበት አደሩ። ሰዎችም ያነጉ ጊዜ ሁሉም ባንዲራው እንዲሰጠው ተስፋ በማድረግ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ማልደው ሄዱ። እርሳቸውም "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ የት አለ? አሉ። ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አይኑን አሞታል" ተባሉ። እርሳቸውም "ሰው ላኩበት!" አሏቸው። እርሱም ተይዞ መጣና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዓይኑ ላይ ተፉና ዱዓ አደረጉለት። እርሱም ከዚህ በፊት ምንም በሽታ እንዳልነበረበት ሆኖ ተፈወሰ። ባንዲራውንም ሰጡት። ዐሊይም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንደኛው አምሳያ እስኪሆኑ ድረስ ልዋጋቸውን?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም አሉት: "ቀያቸው እስክትሰፍር ድረስ ተረጋግተህ ተጓዝ። ቀጥሎ ወደ እስልምና ጥራቸው። በነርሱ ላይ ግዴታ የሚሆንባቸውንም የአላህ ሐቅ ንገራቸው። በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።