Skip to content

«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።»

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።»

كان رسولُ الله صلى الله عليه وسلم إذا عَطَس وضَعَ يَدَه -أو ثوبَهُ- على فيهِ، وخَفَضَ -أو غضَّ- بها صوتَهُ.

አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ: መጀመሪያ: ከአፋቸው ወይም ከአፍንጫቸው አንዳች ነገር ወጥቶ አብሯቸው የተቀመጠውን ላለማወክ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ ያኖራሉ። ሁለተኛ: ድምፃቸውን ይቀንሱ ነበር። ከፍም አያደርጉትም።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በማስነጠስ ዙሪያ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መመሪያ መገለፁና በዚህ ጉዳይ እርሳቸውን መከተል እንደሚገባ እንረዳለን።

አንድ ሰው ያስነጠሰ ጊዜ ከርሱ አንዳች ነገር ወጥቶ አብሮ የተቀመጠውን እንዳያውክ ልብስን ወይም መሀረብና የመሳሰሉትን አፍና አፍንጫ ላይ ማኖር እንደሚወደድ እንረዳለን።

ሲያስነጥሱ ድምፅን ዝግ ማድረግ የሚፈለግ ጉዳይ ነው። ይህም ስነ-ስርዓትን ከሚያሟሉና ከመልካም ስነ‐ምግባር የሚመደብ ነው።

ማጣቀሻዎች

ሱነን አቡዳውድ (7/ 375) (5029).

ሱነን ቲርሚዚ (4/ 461) (2745).

ሙስነድ አሕመድ (15/ 412) 9662).

ተጨማሪ (9)

شرح رياض الصالحين.

لابن عثيمين (4/ 440).

تطريز رياض الصالحين.

لفيصل آل مبارك (ص528).

بهجة الناظرين.

لسليم الهلالي (2/ 149).

نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.

لمجموعة من الباحثين (1/ 678).

كنوز رياض الصالحين لمجموعة من الباحثين (11/ 432).