Skip to content

እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና

ከጃቢር አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው፦

አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና “አዎን!” አሉት። እሱም፦ "በዚህ ላይ አንድንም ላልጨምር በአላህ እምላለሁ! " አለ።

أَنَّ رَجُلًا سَأَلَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: أَرَأَيْتَ إِذَا صَلَّيْتُ الصَّلَوَاتِ الْمَكْتُوبَاتِ، وَصُمْتُ رَمَضَانَ، وَأَحْلَلْتُ الْحَلَالَ، وَحَرَّمْتُ الْحَرَامَ، وَلَمْ أَزِدْ عَلَى ذَلِكَ شَيْئًا، أَأَدْخُلُ الْجَنَّةَ؟ قَالَ: «نَعَمْ»، قَالَ: وَاللهِ لَا أَزِيدُ عَلَى ذَلِكَ شَيْئًا.

ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ከዚህም ሱና ፆሞችን ያልጨመረ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

አንድ ሙስሊም መጨረሻው ጀነት መግባት እንዲሆን፥ ግዴታዎችን በመተግበር እና ክልከላን በመተው ላይ ጥረት ሊኖረው ይገባል ።

ሐላል ፍቁድ ነገሮችን ፍቁድነታቸውን በማመን መተግበርና ክልክል ነገሮችን ክልክልነታቸውን በማመን መራቅ አሳሳቢ (ወሳኝ) ጉዳይ መሆኑን ፤

ግዴታዎችን መፈፀምና ክልክሎችን መተው ጀነት መግቢያ (ሰበብ) ምክንያት ነው።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 44) (15).

ተጨማሪ (3)

جامع العلوم والحكم (1/513).

شرح الأربعين النووية للعثيمين (ص: 215).

فتح القوي المتين في شرح الأربعين للعباد (ص 77).