"ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ጋር ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»
«مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَاللهُ فِي عَوْنِ الْعَبْدِ مَا كَانَ الْعَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهِ، وَمَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّةِ، وَمَا اجْتَمَعَ قَوْمٌ فِي بَيْتٍ مِنْ بُيُوتِ اللهِ يَتْلُونَ كِتَابَ اللهِ وَيَتَدَارَسُونَهُ بَيْنَهُمْ إِلَّا نَزَلَتْ عَلَيْهِمِ السَّكِينَةُ، وَغَشِيَتْهُمُ الرَّحْمَةُ، وَحَفَّتْهُمُ الْمَلَائِكَةُ، وَذَكَرَهُمُ اللهُ فِيمَنْ عِنْدَهُ، وَمَنْ بَطَّأَ بِهِ عَمَلُهُ لَمْ يُسْرِعْ بِهِ نَسَبُهُ».
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሙስሊም አላህ ዘንድ የሚመነዳው ከሙስሊሞች ጋር ከሚሰራው የስራ አይነት አንፃር እንደሆነ ገለፁ። ከአንድ አማኝ ላይ ከዱንያ ችግሮች መካከል አንድን ችግርና መከራ ያቀለለ፣ የገላገለ፣ ያስወገደና ያነሳ ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮች መካከል አንድን ችግሩን በማቅለል ይመነዳዋል። ለተቸገረ ያቀለለ፣ ያገራ፣ ችግሩንም ያስወገደ አላህም ለርሱ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ጉዳዩን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር - ለምሳሌ ግልፅ መውጣት የማይገባውን ስህተትና ጥፋት እርሱ ላይ አይቶ - የሸሸገለት ሰው አላህ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ነውሩን ይሸሽግለታል። አንድ ሰው ወንድሙን ዲናዊም ይሁን ዱንያዊ ጥቅሞቹ ላይ እስካገዘው ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ይሆናል። ማገዝ በዱዓ፣ በአካል፣ በገንዘብና ከዚህም ውጪ ባሉ ነገሮች ይፈፀማል። የአላህን ፊት ፈልጎበት ሸሪዓዊ ዕውቀትን ለማግኘት የተጓዘን ሰው ወደ ጀነት የሚያደርሰውን መንገድ አላህ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ዘንድ ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ ከተሰባሰቡ በነርሱ ላይ እርጋታና ስክነት ይሰፍናል፤ የአላህ እዝነትም ይሸፍናቸዋል፤ መላዕክቶች ያካብቧቸዋል፤ አላህ ዘንድ ቅርብ ከሆኑት ጋር ያሞግሳቸዋል (ያወድሳቸዋል)። አላህ ባሪያውን በላይኛው አለም ማውሳቱ ብቻ ከክብር በቂ ነው። ስራው ጎዶሎ የሆነ ሰው የተሟላ ስራ የሰሩ ሰዎች ደረጃ ላይ አይደርስም። ስለዚህ በዘር ልቅናና በወላጆች ደረጃ ተማምኖ መልካም ስራን ማጓደል አይገባም።
ኢብኑ ደቂቅ አልዒዲ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ትልቅና የተለያዩ ዕውቀቶችን፣ መርሆችንና ስነስርዓቶችን የጠቀለለ ሐዲሥ ነው። ይህ ሐዲሥ ሙስሊሞችን ጉዳያቸውን በመፈፀምና በተቻለው መጠን በዕውቀት ወይም በገንዘብ ወይም በእገዛ ወይም ጠቃሚን ነገር በመጠቆም ወይም በምክር ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች ሁሉ መጥቀም እንደሚገባ ያስረዳናል።"
ለተቸገረ ሰው ችግሩን በማቅለል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሙስሊምን በማገዝ ላይ መነሳሳቱንና ወንድሙን ባገዘበት ልክም አላህም አጋዡን ሰው እንደሚያግዘው እንረዳለን።
ሙስሊምን ከመሸሸግ መካከል ነውሩን አለመከታተል አንዱ ነው። ከሰለፎች ከአንዱ እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል "ነውር የሌለባቸው ሰዎች አጋጥመውኛል። የሌሎችን ነውር ያወሩ እለት ግን ሰዎችም የነርሱን ነውር አወሩባቸው። ነውር የነበረባቸው ሰዎችም አጋጥመውኛል። የሰዎችን ነውር ከማውራት የተቆጠቡ እለት ነውራቸውም ተረሳች።"
የሰዎችን ነውር መሸሸግ ማለት እነርሱን አለመምከርና እንዲለወጡ አለማድረግ ማለት አይደለም። ይልቁንም ከመሸሸግም ጋር እንለውጠዋለን። ይህም ማበላሸትና ጥመት ላይ በመዘውተሩ መገለጫው እስኪሆን የደረሰውን አይመለከትም። በዚህ ባህሪ የታወቀ ከሆነ ግን የርሱን ነውር መሸሸግ አይወደድም። ይልቁንም የባሰ መዘዝ እንዳይመጣ ስጋት እስከሌለ ድረስ በርሱ ጉዳይ እርምጃ መውሰድ ወደሚችል ሰው እንወስደዋለን። ይህም ለርሱ ነውሩን መሸሸግ በማበላሸቱ ላይ እንዲታለል፤ ሰዎችን ወደ ማወክ እንዲያመራ ስለሚያደርግና ከርሱ ውጪ ያሉ የክፋትና የአመፅ ባለቤቶችንም ስለሚያደፋፍር ነው።
ዕውቀትን በመፈለግ፣ ቁርአንን በማንበብና በመማማር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: ይህ ሐዲሥ መስጂድ ውስጥ ቁርአንን ለማንበብ መሰብሰብ ያለውን ትሩፋት ይጠቁማል። ... መድረሳ ውስጥ፣ ዛውያና የመሳሰሉት ውስጥ መሰባሰብም ኢንሻአላህ (በአላህ ፈቃድ) ይህን ደረጃ እንደሚያስገኝ ተስፋ እናደርጋለን።
አላህ ምንዳን ያስቀመጠው በተግባር ነው እንጂ በዘር አይደለም።
ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 2074) (2699).
ተጨማሪ (6)
التحفة الربانية.
لإسماعيل الأنصاري (ص82).
الأحاديث الأربعون النووية وعليها الشرح الموجز المفيد.
لعبد الله المحسن (ص69).
شرح الأربعين النووية.
لابن عثيمين (ص355).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
32 መጻሕፍትተጨማሪ (32)
- الله -جل جلاله- أنيس المحبين وملاذ القاصدين«مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا؛ نَفَّسَ اللهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمَ القِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ؛ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ»
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“مَن سَلَك طريقا يلتمس فيه علما سهّل الله له به طريقا إلى الجنة، وما اجتمع قوم في بيت من بيوت الله، يتلون كتاب الله، ويتدارسونه بينهم، إلا نزلت عليهم السكينة، وغشيتهم الرحمة، وحفتهم الملائكة، وذكرهم الله فيمن عنده”.
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“من نفس عن مؤمن كربة من كرب الدنيا نفس الله عنه كربة من كرب يوم القيامة، ومن يسر على معسر يسر الله عليه في الدنيا والآخرة، ومن ستر مسلما ستره الله في الدنيا والآخرة، والله في عون العبد ما كان العبد في عون أخيه”.
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“ما اجتمع قوم في بيت من بيوت الله تعالى يتلون كتاب اللّه ويتدارسونه بينهم، إلا نزلت عليهم السكينة، وغشيتهم الرحمة، وحفتهم الملائكة، وذكرهم الله فيمن عنده”.
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“من نفّس عن مؤمن كربة من كرب الدنيا نفس الله عنه كربة من كرب يوم القيامة، ومن يسرّ على معسر يسر الله عليه في الدنيا والآخرة، ومن ستر مسلما ستره الله في الدنيا والآخرة، والله في عون العبد ما كان العبد في عون أخيه”.
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 1 «وَاللهُ فِي عَوْنِ الْعَبْدِ مَا كَانَ الْعَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهُ»،
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 2وَمَنْ يَسَّرَ عَلَىٰ مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ في الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ،
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 5«وما اجتمعَ قومٌ في بيتٍ من بيوتِ اللهِ يتلُون كتابَ الله، ويَتَدارَسُونَه بينَهُم، إلَّا نَزَلَتْ عليهِمُ السَّكينةُ، وغشيتْهمُ الرَّحْمةُ، وحَفَّتْهمُ الملائكةُ، وذَكَرَهُمُ اللهُ فيمَنْ عندَه».
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 6«وَمَنْ سَلَكَ طريقاً يلتمسُ فيه علماً سهَّلَ اللهُ لهُ به طريقاً إلىٰ الجَنَّة».
- شرح الأربعين النووية«مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللَّهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ، يَسَّرَ اللَّهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَ
- ما لا يسع أطفال المسلمين جهله«وَاللَّهُ فِي عَوْنِ العَبْدِ مَا كَانَ العَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهِ»[92].
- مادة العقيدة الإسلامية(مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللَّهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللَّهُ عَلَيْهِ في الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ ال
- مجالس تدارس القرآن للمبتدئين (سورة الفاتحة وقصار المفصّل)1«من سلك طريقا يلتمس فيه علما سهل الله له به طريقا إلى الجنة»([35])،
- مجموعة زاد التفسير (1)التفسير 1«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد التربية الإسلامية (1)، والسيرة النبوبة (1)، والعقيدة (1)، والفقه (1)التربية الأسلامية 1«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد التربية الإسلامية (1)، والسيرة النبوبة (1)، والعقيدة (1)، والفقه (1)2«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد التربية الإسلامية (3)، والسيرة النبوية (3)التربية الإٍسلامية -3- «من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد التربية الإسلامية (4)التربية الإسلامية 4«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد التفسير (2)التفسير 2«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد الحديث (1)الحديث 1«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد الحديث(2)1«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد الحديث(2)1«مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا، نَفَّسَ الله عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ، يَسَّرَ الله عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ ال
- مجموعة زاد الحديث(2)1(سَهَّلَ الله لَهُ بِهِ طَريقًا إِلَى الجَنَّةِ)
- مجموعة زاد الحديث(2)1(ومن بطَّأ به عملُهُ لم يسرِعْ به نسبُهُ)
- مجموعة زاد الحديث(2)1(مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً...)
- مجموعة زاد الحديث(3)1«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد العقيده (4)العقيدة 4«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مجموعة زاد الفقه (3)الفقه 3«من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا سهل الله له به طريقًا إلى الجنة»
- مشروع منهاج زادكزادك 3 طالب نهائي«مَا اجْتَمَعَ قَوْمٌ فِي بَيْتٍ مِنْ بُيُوتِ اللهِ يَتْلُونَ كِتَابَ اللهِ، وَيَتَدَارَسُونَهُ بَيْنَهُمْ إِلَّا نَزَلَتْ عَلَيْهِمِ السَّكِينَةُ، وَغَشِيَتْهُمُ الرَّحْمَةُ، وَحَفَّتْهُمُ الْمَلَائِكَةُ، وَذَكَرَهُمُ اللهُ فِيمَنْ عِنْدَه
- نبراس طالب (1)1«مَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ»
- نبراس طالب (1)1«مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُسْلِمٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ ال
- نبراس طالب (3)نبراس طالب 3«وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ»