"አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
ከሸዳድ ቢን አውስ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: ሁለቱን ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ሸምድጃለሁ፦
"አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል። የገደላችሁ ጊዜ አገዳደላችሁን አሳምሩ፤ ያረዳችሁም ጊዜ አስተራረዳችሁን አሳምሩ። አንዳችሁ ቢላውን ይሞርድ እርዱንም ይገላግለው።"
«إِنَّ اللهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ، فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ».
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ በኛ ላይ በሁሉም ነገሮች ኢሕሳንን ግዴታ እንዳደረገ ተናገሩ። ማሳመር (ኢሕሳን) ማለት በአምልኮውም ውስጥ፣ መልካምን ሲፈፅምም፣ ከፍጡራን ላይ ጎጂን ነገር ሲያስወግድም ዘውትር አላህ ያየኛል ማለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በመግደልና በማረድ ውስጥ ማሳመርም አንዱ ነው። በመግደል ኢሕሳን ሲባል በቂሷስ (ሸሪዐዊ የቅጣት ብይን ለምሳሌ የገደለ መገደል) ተፈፃሚነት ወቅት: ለመግደል ገሩን፣ ቀላሉንና የተገዳዩን ነፍስ በፍጥነት ሊያወጣ የሚችለውን መንገድ በመምረጥ ነው። በእርድ ማሳመር ሲባል ደግሞ እንስሳ በምናርድበት ወቅት ነው። ይህም መሳሪያውን በደንብ በመሞረድ ፣ የሚታረደው እንስሳ እያየ ፊት ለፊቱ ባለመሞረድና ሌላ እርዱን የሚመለከት እንስሳ ቦታው ላይ እያለ ባለማረድ ለእንስሳ በማዘን ነው።
الشفرة: السكين العريضة.
የላቀውና የተከበረው አላህ በፍጡራኑ ላይ ያለው እዝነትና ርህራሄን እንረዳለን።
አገዳደልና አስተራረድ ላይ ኢሕሳን የሚባለው ሸሪዐውን የተከተለ (የዋጀ) በሆነ መልኩ ሲፈፀም ነው።
ሸሪዐ ምሉዕና ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ሲሆን ከዚህም መካከል ለእንስሳት ማዘኑና መራራቱ አንዱ ነው።
የሰውን ልጅ ከገደሉ በኋላ ሰውነቱን መቆራረጥ መከልከሉን እንረዳለን።
እንስሳትን ማሰቃየት ያለበት ነገር ሁሉ ክልክል መሆኑን ተረድተናል።
ሶሒሕ ሙስሊም (3/ 1548) (1955).
ተጨማሪ (8)
التحفة الربانية في شرح الأربعين حديثا النووية (ص38).
شرح الأربعين النووية.
لابن عثيمين (ص185).
فتح القوي المتين في شرح الأربعين وتتمة الخمسين.
للعباد (ص65).
فتح الباري.
لابن حجر (9/ 644).
شرح النووي على مسلم (13/ 107).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
5 መጻሕፍት- ሀድይ፣ ኡዱሒያና እርድን የተመለከቱ ህግጋትأحكام الهدي والأضاحي والتذكية "አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (አሳምሮ ማድረግን) ጽፏል (ደንግጓል)። የገደላችሁም ጊዜ አገዳደላችሁን አሳምሩ፤ ያረዳችሁም ጊዜ አስተራረዳችሁን አሳምሩ። አንዳችሁ ቢላውን ይሞርድ እርዱንም ይገላግለው።" [8]
- ስለ እስልምና አጭር ገለፃ፤ በተከበረው ቁርአን እና በነብያዊ ሐዲሥ በመጣበት መልኩ«አላህ ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እንዲከናወን ወስኗል፤ ስለዚህ መግደል ካለባችሁ እንኳ በጥሩው ዘዴ ፈፅሙት (ስትገድሉ አገዳደላችሁን አሳምሩ)፤ እንስሳን ስታርዱ በጥሩ ሁኔታ እረዱ፤ ማለትም: እያንዳንዳችሁ ቢላዋን ይሳለው አድርጉ እና እንስሳውን በተቻለ መጠን ትንሽ ፋታ ስጡት።»
ተጨማሪ (3)
- الحديث زاد 4الحديث 4«إِنَّ الله كَتَبَ الإِحْسانَ على كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا القِتْلَةَ، وَإِذا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ، وَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ».
- رسالة موجزة عن الإسلام كما جاء في القرآن الكريم والسنة النبوية (مشتملة على الأدلة)رِسَالَةٌُ مُوجَزَةٌُ عَنِ الْإِسْلَامِ كَمَا جَاءَ فِي الْقُرْآنِ الْكَرِيمِ وَالسَّنَةِ النَّبَوِيَّة-مشتملة على الأدلة -للحرمين-«إنَّ اللَّهَ كَتَبَ الإحْسَانَ علَى كُلِّ شيءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فأحْسِنُوا القِتْلَةَ، وإذَا ذَبَحْتُمْ فأحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ، فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ» [39].
- نبراس طالب (2)نبراس طالب (2) «إِنَّ اللهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ، وَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ»