Skip to content

'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'"

ከቡረይደህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'"

«إِنَّ الْعَهْدَ الَّذِي بَيْنَنَا وَبَيْنَهُمُ الصَّلَاةُ، فَمَنْ تَرَكَهَا فَقَدْ كَفَرَ».

ቲርሚዚ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሙስሊሞችና በሌሎች ከሀዲያንና መናፍቃን መካከል ያለው መተማመኛና ቃል ኪዳን ሶላት እንደሆነና ሶላትን የተወ ሰውም በርግጥ እንደካደ ገለፁ።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የሶላት ጉዳይ ትልቅ እንደሆነና በአማኝና በከሀዲ መካከል መለያም እንደሆነ እንረዳለን።

የሙስሊምነት ፍርድ በሰውዬው ውስጣዊ ማንነት ላይ ሳይሆን ውጫዊ ማንነቱ ላይ በመንተራስ እንደሚፀና እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሱነኑ ነሳኢይ (1/ 231) (463).

ሱነን ቲርሚዚ (4/ 365) (2621).

ሱነን ኢብኑ ማጀህ (2/ 181) (1079).

ሙስነድ አሕመድ (38/ 20) (22937).

ተጨማሪ (2)

فيض القدير (4/ 395).

ذخيرة العقبى في شرح المجتبى (6/ 192) (6/ 193).