Skip to content

"(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።"

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦

"(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።"

«مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ»

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የረመዳንን ወር በአላህ አምኖ፣ በፆም ግዴታነትና አላህ ለፆመኞች ያዘጋጀውን የደለበ ምንዳና አጅር እውነት ብሎ እንዲሁም ፆሙም ለይዩልኝና ይስሙልኝ ሳይሆን የአላህን ፊት ፈልጎበት የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉን እንደሚማር ነገሩን።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በረመዳን ፆምም ይሁን በሌሎች መልካም ስራዎች ላይ ኢኽላስ ያለውን ትሩፋትና አንገብጋቢነትን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 16) (38).

ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 523) (760).

ተጨማሪ (8)

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (2/ 361).

نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.

لمصطفى الخِن وغيره (2/ 868).

كنوز رياض الصالحين.

لمجموعة من الباحثين (15/ 40).

شرح رياض الصالحين.

لابن عثيمين (5/ 270).