Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
‹ሶላትን መስገድ የፈለጋችሁ ጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ። ከዚያም አንድ ሰው ይምራችሁ። ኢማሙ ተክቢራ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጉ! ፣ {غَيرِ المَغضوبِ عَلَيهِم وَلَا الضّالّينَ} [አልፋቲሐ:7] ያለ ጊዜ አሚን በሉ አላህ ይቀበላችኋልና፤ ተክቢራ አድርጎ ሩኩዕ ያደረገ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጋችሁ ሩኩዕ አድርጉ። ኢማሙ ከናንተ በፊት ሩኩዕ ያድርግ ከናንተ በፊትም ቀና ይበል።› የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህም አሉ "ይህቺ (ኢማሙ ቀና ያለበት ቅፅበት) በዚህች (እናንተ ከኢማሙ ከዘገያችሁበት) ጋር ይካካሳል ፤ ኢማሙ 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' ያለ ጊዜ 'አላሁመ ረበና ለከል ሐምድ' በሉ። አላህ ይሰማችኋልና። የጠራውና ከፍያለው አላህ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት 'ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ' 'አላህ ያመሰገነውን ሰሚ ነው' ብሏልና። ኢማሙ ተክቢራ አድርጎ ሱጁድ የወረደ ጊዜ እናንተም ተክቢራ አድርጋችሁ ሱጁድ ውረዱ። ኢማሙ ከናንተ በፊት ሱጁድ ይውረድ ከናንተ በፊትም ቀና ይበል። የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህም አሉ 'ይህቺ (ኢማሙ ሱጁድ ሲወርድ የቀደማቹ ቅፅበት) በዚህች (እናንተ እርሱ ቀና ሲል በምትዘገዩት ቅፅበት) ይካካሳል።' የምትቀመጡበት በሆነ ወቅት የአንዳችሁ የመጀመሪያ ቃሉ 'አትተሒይያቱ፣ አጥጦይዪባቱ፣ አስሶለዋቱ ሊላሂ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢዩ ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ አስሰላሙ ዐለይና ወዐላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' ይሁን። ትርጉሙም 'ክብሮች ባጠቃላይ፣ ጥሩ ነገሮች ባጠቃላይ፣ ሶላቶች ባጠቃላይ ለአላህ የተገቡ ናቸው። አንቱ ነቢይ ሆይ ሰላም፣ የአላህ እዝነትና በረከቱ በርሶ ላይ ይሁን። ሰላም በኛ ላይና በአላህ ደጋግ ባሮች ላይም ይስፈን። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ። ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልዕክተኛው መሆናቸውንም እመሰክራለሁ።' ማለት ነው።›"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሰውዬ ከሰልፍ ኋላ ብቻውን ሲሰግድ ተመለከቱትና ሶላቱን እንዲደግመው አዘዙት።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።