Skip to content

"ዓኢሻ ሆይ! አላህ ርህሩህ ነው። ለስላሳነትንም ይወዳል። አላህ በግትርነት ላይና ከልስላሴ ውጪ ባሉ መስተጋብሮች ላይ የማይሰጠውንም በልስላሴ ይሰጣል።"

የነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባለቤት ከሆነችው ከአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ፦

"ዓኢሻ ሆይ! አላህ ርህሩህ ነው። ለስላሳነትንም ይወዳል። አላህ በግትርነት ላይና ከልስላሴ ውጪ ባሉ መስተጋብሮች ላይ የማይሰጠውንም በልስላሴ ይሰጣል።"

«يَا عَائِشَةُ إِنَّ اللهَ رَفِيقٌ يُحِبُّ الرِّفْقَ، وَيُعْطِي عَلَى الرِّفْقِ مَا لَا يُعْطِي عَلَى الْعُنْفِ، وَمَا لَا يُعْطِي عَلَى مَا سِوَاهُ».

ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለአማኞች እናት ለሆነችው ለዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- በእዝነት ላይ አነሳሷት። አላህ ለባሮቹ ርህሩህና ለስላሳ ነው። ለነርሱ ገርን ይፈልግላቸዋል። ለነርሱ ችግርን አይፈልግም። ከአቅማቸው በላይም አያስገድዳቸውም። የአላህ ባሪያ የሆነም ሰው ገራገር ማንነትን መላበሱንና ገርን መውሰዱን አላህ ይወድለታል። ልበ ደረቅና ስነምግባረ ብልሹ መሆንም የለበትም። አላህ በዱንያ ውስጥ እዝነትና ገራገርነትን ለተላበሰ ሰው ባማረ ሙገሳ ያወሳዋል፣ ፍላጎቱን ያሟላለታል፣ ግቡንም ያሳካለታል። በመጪው ዓለም ደግሞ ትልቅ ምንዳን ይሰጠዋል። ይህም ግትርነት፣ ድርቅናና ሀይለኝነትን ለተላበሰ ሰው ከሚሰጠው የበዛ ምንዳ ነው። ለስላሳነትን መላበስ ሌሎች ባህሪያትን መላበስ የማያመጡትን ጥቅም ይዞ ይመጣል።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በለስላሳነት ላይ መነሳሳቱንና ከግትርነት መከልከሉን እንረዳለን።

ከመልካም ስነምግባሮች መካከል የለስላሳነት ደረጃ የላቀ መሆኑን እንረዳለን።

ልስላሴን የተላበሰ ሰው ከአላህ የሆነ መልካም ሙገሳና ትልቅ ምንዳ የተገባው ይሆናል።

ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ግትርነት የለስላሳት ተቃራኒ ነው። ማለትም ሁለቱንም የዳዕዋ መንገዶች መጠቀም የሚቻልበት ስፍራ ላይ ሰዎችን በልስላሴና በለዘብተኝነት ወደ ቅናቻ የሚጣራ ሰው በግትርነትና በሃይለኝነት ከሚጣራ ሰው ይሻላል። ያለበለዚያ ግን ቦታው በሚመጥነው የዳዕዋ መንገድ ይሰብካል። እውነተኛውን ሁኔታም የሚያውቀው አላህ ነው።"

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 2003) (2593).

ተጨማሪ (4)

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (1/ 683).

المنهاج شرح صحيح مسلم بن الحجاج.

للنووي (16/ 145).