"ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው።
ከአቡ ኡማማ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዐምር ቢን ዐበሳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው ነገረኝ:
"ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"»
«أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الرَّبُّ مِنَ العَبْدِ فِي جَوْفِ اللَّيْلِ الآخِرِ، فَإِنْ اسْتَطَعْتَ أَنْ تَكُونَ مِمَّنْ يَذْكُرُ اللَّهَ فِي تِلْكَ السَّاعَةِ فَكُنْ».
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጥራት የተገባው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ ሲሶ በመሆኑ አንተ አማኝ ሆይ! በዚህ ወቅት ከሚያመልኩት፣ ከሚሰግዱ፣ ከሚያወሱ፣ በወንጀላቸው ከሚፀፀቱ ሰዎች መካከል ለመሆን ከተሳካልህና ከቻልክ በዚህ ወቅት አጅር መሸመትና መታገል የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ተናገሩ።
አንድ ሙስሊም በሌሊቱ የመጨረሻ ወቅት ላይ ዚክር እንዲያደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ዚክር ለማለት፣ ዱዓ ለማድረግና ለመስገድ አንዱ ወቅት ከአንዱ እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
"ጌታ ወደ ባሪያው እጅግ ቅርብ የሚሆነው" በሚለው ሐዲሥና "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሆኖ ነው።" በሚለው ሐዲሥ መካከል ባለው ልዩነት ሚረክ እንዲህ ብለዋል: እዛኛው ላይ የተፈለገው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው የሌሊቱ አጋማሽ ላይ ሲሆን እዚህኛው ላይ የተፈለገው ደግሞ አንድ ባሪያ ካሉት ሁኔታዎች መካከል ወደ ጌታ የሚቀርበው በሱጁድ ሁኔታው መሆኑን ለመግለፅ ነው።
ሱነን ቲርሚዚ (5/ 537) (3579).
ሱነን አቡዳውድ (2/ 454) (1277).
ሱነኑ ነሳኢይ (1/ 279) (572).
ተጨማሪ (8)
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (2/ 1019).
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (5/ 509).
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (17/ 535).
مشكاة المصابيح.
للتبريزي (1/ 387).