Skip to content

ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር

አቢ ዐብዲረሕማን አስሱለሚይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ አሉ፦

ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰሐቦች መካከል ቁርኣን ያስተምረን የነበረ አንድ ሰሐባ "ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር። በዚህም "ዕውቀትንም ተግባርንም ተማርን" አሉ።" ብሎ ነገረን።

حَدَّثَنَا مَنْ كَانَ يُقْرِئُنَا مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُمْ كَانُوا يَقْتَرِئُونَ مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَشْرَ آيَاتٍ، فَلَا يَأْخُذُونَ فِي الْعَشْرِ الْأُخْرَى حَتَّى يَعْلَمُوا مَا فِي هَذِهِ مِنَ الْعِلْمِ وَالْعَمَلِ، قَالُوا: فَعَلِمْنَا الْعِلْمَ وَالْعَمَلَ.

አሕመድ ዘግበውታል።
ሐሰን ነው።
ማብራሪያ

ሰሐቦች -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስር የቁርኣን አንቀፆችን ይቀስሙ ነበር። በቀሰሙት አስር አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀት እስኪረዱና እሱን ሳይተገብሩ ወደ ሌላ እውቀት አይሸጋገሩም ነበር።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ደረጃና ቁርኣንን የመማር ጉጉታቸውን እንረዳለን።

ቁርኣንን መማር የሚባለው በመረዳትና ውስጡ ባለው በመተግበር ነው እንጂ በማንበቡና በመሸምደዱ ብቻ አይደለም።

ዕውቀት ከንግግርና ከተግባር በፊት እንደሆነ ተረድተናል።

ማጣቀሻዎች

ሙስነድ አሕመድ (38/ 466) (23482).