Skip to content

"አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦

"አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል። ካፊር ግን ለአላህ ብሎ በሠራው መልካም ሥራ ምክንያት በዱንያ እንዲበላ ይደረጋል። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ በአኺራ የሚመነዳበት መልካም ሥራ አይኖረውም።"

«إِنَّ اللهَ لَا يَظْلِمُ مُؤْمِنًا حَسَنَةً، يُعْطَى بِهَا فِي الدُّنْيَا وَيُجْزَى بِهَا فِي الْآخِرَةِ، وَأَمَّا الْكَافِرُ فَيُطْعَمُ بِحَسَنَاتِ مَا عَمِلَ بِهَا لِلَّهِ فِي الدُّنْيَا، حَتَّى إِذَا أَفْضَى إِلَى الْآخِرَةِ، لَمْ تَكُنْ لَهُ حَسَنَةٌ يُجْزَى بِهَا».

ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በአማኞች ላይ የዋለውን ትልቅ ችሮታና ከከሀዲያን ጋር ያለውን ፍትሀዊነት ያብራራሉ። አማኝ የሆነ ሰው የመልካም ሥራው ምንዳ ምንም አትጎድልም። በአኺራ ከሚደለብለት (ከሚከማችለት) ምንዳ በተጨማሪ በዱንያም በአምልኮው ምክንያት መልካምን ይሰጠዋል። ይህ ካልሆነ እንኳ ሁሉም ምንዳው ለሱ አኺራ ላይ ይጠበቅለታል። ካፊር ግን ለሠራው መልካም ሥራ የሚመነዳው በዱንያ አላህ በሚሰጠው መልካም ነገር ነው። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ ምንም የሚመነዳው ክፍያ አይኖረውም። ምክንያቱም በመልካም ሥራ በሁለቱም ዓለም ለመጠቀም የግድ ባለቤቱ አማኝ መሆን ይጠበቅበታል።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

በክህደት ላይ የሞተ ሰው ምንም ተግባር አይጠቅመውም።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ ሙስሊም (4/ 2162) (2808).

ተጨማሪ (3)

المفهم لما أشكل من تلخيص كتاب مسلم (1/ 460).

البحر المحيط الثجاج في شرح صحيح الإمام مسلم بن الحجاج (43/ 460).

شرح النووي على مسلم (17/150).