Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 6 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ አንድ ባሪያ በአንድ ቦታ እንዲሞት የወሰነ ጊዜ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድበትን ምክንያት ያደርግለታል።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ የፃፈብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ፅሁፉም ደርቋል።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚይና ሌሎችም ዘግበውታል
"አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአጎታቸው እንዲህ አሏቸው፦ " ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ" አቡ ጣሊብም "የቁረይሾች ማነወር ባልነበር "ለመስለም ያነሳሳው የሞት ፍራቻ ነው" ይላሉ ብዬ ባልሰጋ (እሰልም ነበር)" (ይህ ስጋት ባልነበር) ላ ኢላሀ ኢለላህ በማለት ደስታን አሰርፅልህ ነበር።" አላቸው። አላህም ይህን አንቀፅ አወረደ {አንተ የወደድከውን ሰው ፈፅሞ አታቀናም። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።} [አልቀሶስ: 56]
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።