Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 3 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንተ ዓመቱን ሙሉ እየፆምክ ሌሊቱን ሙሉ ትቆማለህን?" እኔም "አዎ" አልኳቸው። እርሳቸውም "አንተ ይሄንን የምታደርግ ከሆነ አይንህም ይሰረጉዳል ነፍስህም ይደክማል። አመቱን ሙሉ የጾመ አልጾመም። በወር ሶስት ቀን መጾም አመቱን ሙሉ እንደመጾም ነው።" አሉ። እኔም "እኔ ከዚህም በላይ መጾም እችላለሁ።" አልኩኝ። እርሳቸውም "የዳውድን ዐለይሂ ሰላም ጾም ፁም! ዳውድ ዐለይሂ ሰላም አንድ ቀን እየጾመ አንድ ቀን ይፈታ ነበር። ጠላትን ጦር ሜዳ የተገናኘ ጊዜም አይሸሽም ነበር።" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ፍፁም ወዳጄ የሆኑት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል። ከሁሉም ወር ሶስት ቀናት በመጾም፣ የዱሓን ሁለት ረከዓ በመስገድና ከመተኛቴ በፊት ዊትር በመስገድ አደራ ብለውኛል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።