Skip to content

"በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።"

ከዐብደሏህ ቢን ዓምር (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡

"በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።"

«مَنْ قَتَلَ مُعَاهَدًا ‌لَمْ ‌يَرَحْ ‌رَائِحَةَ الْجَنَّةِ، وَإِنَّ رِيحَهَا تُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ أَرْبَعِينَ عَامًا».

ቡኻሪ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙዓሀድን በገደለ ሰው ላይ ያለበትን ከባድ ዛቻ ገለፁ። ሙዓሀድ ማለት ከከሀዲያን መካከል በቃል ኪዳንና በደህንነት ከለላ ወደ ኢስላም ሀገር የገባ ነው። እሱን የገደለ የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት ነው።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ከከሀዲያን መካከል "ሙዓሀድን" ፣ "ዚሚይን" እና "ሙስተእመንን" መግደል ክልክልና ከትላልቅ ወንጀል የሚመደብም ነው።

"ሙዓሀድ" ማለት: ከከሀዲያን መካከል በሀገሩ እየኖረ ሙስሊሞችን ላይዋጋ እነሱም ላይዋጉት ከሙስሊሞች ጋር ቃል ኪዳን የተጋባ ነው። "ዚሚይ" ማለት: በሙስሊሞች ሀገር እንደሀገሩ እየኖረ ግብር የሚከፍል ነው። "ሙስተእመን" ማለት ደግሞ ለተወሰነ ወቅት በቃል ኪዳንና ደህንነት ከለላ ወደ ሙስሊሞች ሀገር የገባ ሰው ነው።

ከሙስሊሞች ውጪ ካሉ ጋር ቃል ኪዳንን ማፍረስ መከልከሉን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች
ተጨማሪ (8)

صحيح البخاري منحة العلام في شرح بلوغ المرام.

لعبد الله الفوزان (8/ 232).

توضيح الأحكام شرح بلوغ المرام.

للبسام (6/ 90).

فتح ذي الجلال والإكرام بشرح بلوغ المرام.

لابن عثيمين (5/ 520).

سبل السلام.

لمحمد الصنعاني (2/ 501).