«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ"
ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ይሉ ነበር።» ትርጉሙም "ጌታችን ሆይ! ከምስጋና ጋር ጥራት የተገባህ ነህ! አላህ ሆይ! ማረኝ።" ማለት ነው። ከእናታችን ዓኢሻ እንደተላለፈው እንዲህም ብላለች: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቁርአን ላይ የመጣውን ትእዛዝ ወደ ተግባር ለመለወጥ በሩኩዓቸውና በሱጁዳቸው ወቅት "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ማለትን ያበዙ ነበር።
مَا صَلَّى النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ صَلاَةً بَعْدَ أَنْ نَزَلَتْ عَلَيْهِ: {إِذَا جَاءَ نَصْرُ اللَّهِ وَالفَتْحُ} [النصر: 1] إِلَّا يَقُولُ فِيهَا: «سُبْحَانَكَ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي». وعَنْها قَالَتْ: كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُكْثِرُ أَنْ يَقُولَ فِي رُكُوعِهِ وَسُجُودِهِ: «سُبْحَانَكَ اللهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللهُمَّ اغْفِرْ لِي» يَتَأَوَّلُ الْقُرْآنَ.
የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተናገረችው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} የሚለው ምዕራፍ የወረደላቸው ጊዜ ቁርአኑን ወደ ተግባር ለመለወጥ {ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው! ምህረትንም ለምነው።} የሚለውን የአላህን ትእዛዝ ፈጥነው ለመፈፀም በሶላት መሀል በሩኩዓቸውና በሱጁዳቸው ወቅት እንዲህ ማለትን ያበዙ ነበር፡ "ሱብሓነከ" ለአንተ ከማይመጥን ከሁሉም ጉድለት አንተን አጠራኸለሁ። "አልላሁምመ ረበና ወቢሐምዲክ" ዛትህ፣ ባህሪህና ድርጊትህ ምሉዕ ስለሆነ ምስጉን በሆኑ ውዳሴዎች አወድስሃለሁ። "አልላሁምመግፊርሊ" ከኔ ላይ ወንጀሌን አብስ! ይቅር በለኝ።
በሩኩዕና በሱጁድ ወቅት ይህን ዱዓ ማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
በእድሜ መጨረሻ ወቅት ምህረት መጠየቅ እንደሚገባ እንረዳለን። ልክ እንደዚሁ አምልኮ ውስጥ የተከሰቱ ጉድለቶች እንዲሟሉም አምልኮዎችን (በተለይም ሶላትን) ምህረትን በመጠየቅ እንድናጠናቅቅ ያስገነዝባል።
ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ ወደ አላህ ከምንቃረብባቸው ነገሮች መካከል ያማረው መመስገኛዎቹን ማውሳትና እርሱን ከጉድለቶችና ነውሮች የጠራና የፀዳ መሆኑን ማውሳት ነው።
አላህን ምህረት መጠየቅ ያለው ትሩፋትና በሁሉም ሁኔታዎች ተፈላጊ መሆኑን እንረዳለን።
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አምልኮ የተሟላ መሆኑንና የአላህንም ትእዛዝ በተሟላ መልኩ መተግበራቸውን እንረዳለን።
ሶሒሕ አልቡኻሪ (6/ 178) (4968.
4967).
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 350-351) (484).
ተጨማሪ (10)
تيسير العلام.
للبسام (ص214).
تنبيه الأفهام.
للعثيمين (2/ 278).
الإفهام في شرح عمدة الأحكام.
لابن باز (ص263).
الإلمام بشرح عمدة الأحكام.
لإسماعيل الأنصاري (1/ 176).
خلاصة الكلام.
فيصل المبارك (ص97).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
16 መጻሕፍትተጨማሪ (15)
- الذكر والدعاء والعلاج بالرقي من الكتاب والسنة"سبحانك اللهم ربنا وبحمدك اللهم اغفر لي".
- الذكر والدعاء والعلاج بالرقي من الكتاب والسنة"سبحانك اللهم ربنا وبحمدك، اللهم اغفر لي".
- تطبيق القرآن والأذكارأذكار الصلاة((سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي))[58].
- تطبيق القرآن والأذكارأذكار الصلاة((سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي)) [66].
- حصن المسلم من أذكار الكتاب والسنةحصن المسلم«سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي»[58].
- حصن المسلم من أذكار الكتاب والسنةحصن المسلمسُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي
- حصن المسلم من أذكار الكتاب والسنةحصن المسلم«سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي» [66].
- حصن المسلم من أذكار الكتاب والسنةحصن المسلمسُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي
- رسالة في الأذكار1كان النبي صلى الله عليه وسلم يُكْثِرُ أن يقول في ركوعه وسجوده: «سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي» يَتأوَّلُ القرآن.
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 1 «سبحانك اللهم ربنا وبحمدك، اللهم اغفر لي».
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 7«سبحانكَ اللّهم ربَّنَا وبحمدِكَ، اللّهم اغْفرْ لي».
- صلاتنا الخاشعة"سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي" ([22])
- من الأحكام الفقهية في الطهارة والصلاة والجنائز«سُبْحَانَكَ الْلَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، الْلَّهُمَّ اغْفِرْ لِي» [38]،
- من الأحكام الفقهية في الطهارة والصلاة والجنائز«سُبْحَانَكَ الْلَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، الْلَّهُمَّ اغْفِرْ لِي» [42]،
- موسوعة الأسئلة (المجموعة الأولى)«سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي»