Skip to content

የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'"

ከቡረይዳህ ቢን ሑሰይብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦

"የዐስርን ሰላት ወቅቱ እንደገባ ቶሎ ስገዱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና: ' የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'"

بَكِّرُوا بِصَلَاةِ الْعَصْرِ، فَإِنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «مَنْ تَرَكَ صَلَاةَ الْعَصْرِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُ».

ቡኻሪ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዐስርን ሶላት ሆን ብሎ ወቅቱን ከማዘግየት አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ ሰው ስራው ተበላሽቶ ከንቱ ይቀራል።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የዐስርን ሶላት በመጀመሪያ ወቅቱ በመጠባበቅ ላይና ወደዚህ ተግባር በመቻኮል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

የዐስርን ሶላት በተወ ሰው ላይ ብርቱ ዛቻ መምጣቱንና ዐስርን ከወቅቱ ማሳለፍ ሌሎችን ሶላቶች ከወቅቱ ከማሳለፍ የበለጠ እጅግ ከባድ መሆኑን እንረዳለን። የዐስር ሶላት {በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡} [አልበቀራህ: 238] በሚለው የአላህ ንግግር ላይ ባለው ትእዛዝ ልዩ ሆና የተወሳች ምርጧ ሶላት ናትና።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 115) (553).

ሙስነድ አሕመድ (38/ 152) (23045).

ተጨማሪ (9)

شرح رياض الصالحين.

لابن عثيمين (5/ 56).

نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.

لمصطفى الخِن وغيره (2/ 777).

فيض القدير شرح الجامع الصغير (3/ 206).

بهجة الناظرين.

لسليم الهلالي (2/ 260).

تطريز رياض الصالحين.

لفيصل آل مبارك (ص614).