«"ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው።
ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፡
«"ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው። ወደኔ የተጠላውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ እጅግ የራቀው እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራ፤ ለአንደበተ ርቱእነት ንግግር የሚያበዛና ሙተፈይሂቆች ናቸው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራንና ለአንደበተ ርቱዕነት ንግግር የሚያበዛን አውቀናል። መተፈይሂቆች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "ኩራተኞች ናቸው።" አሉ።»
«إِنَّ مِنْ أَحَبِّكُمْ إِلَيَّ وَأَقْرَبِكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ القِيَامَةِ أَحَاسِنَكُمْ أَخْلاَقًا، وَإِنَّ أَبْغَضَكُمْ إِلَيَّ وَأَبْعَدَكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ القِيَامَةِ الثَّرْثَارُونَ وَالمُتَشَدِّقُونَ وَالمُتَفَيْهِقُونَ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، قَدْ عَلِمْنَا الثَّرْثَارُونَ وَالمُتَشَدِّقُونَ فَمَا الْمُتَفَيْهِقُونَ؟ قَالَ: «الْمُتَكَبِّرُونَ».
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: ዱንያ ውስጥ ወደኔ ተወዳጁ፤ የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሆነው ስነምግባሩ ያማረ ነው። ዱንያ ውስጥ ወደኔ የተጠላው የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ የራቀው መጥፎ ስነምግባር ያለው፤ (ሠርሣሮች) ከእውነት ለመውጣት ከአቅሙ በላይ እየተጣጣረ ንግግር የሚያበዛ፤ (ሙተሸዲቆች) ያለምንም ጥንቃቄ አንደበተ ርቱዕ ለመባልና ንግግሩን ለማላቅ ንግግሩን የሚያሰፋ፤ እና (ሙተፈይሂቆች) ናቸው። ሶሐቦችም የአላህ መልክተኛ ሆይ! "ሠርሣሮች" እና "ሙተሸዲቆች"ን አውቀናል። "ሙተፈይሄቆች" ማን ናቸው? አሉ። እርሳቸውም: "ኩራተኞች፣ ንግግራቸውን በማስፋትና በንግግራቸው አፋቸውን በመክፈት በሰዎች ላይ የሚያፌዙ ናቸው።" አሉ።
መልካም ስነምግባር የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ውዴታንና የትንሳኤ ቀን ወደርሳቸው መቅረብን ከሚያመጡ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።
መልካም ስነምግባር ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው። መጥፎ ስነምግባር ደግሞ በተቃራኒ ነው።
ስነምግባርን በማሳመር፤ በመተናነስ፣ ጨካኝ ባለመሆንና ያለአቅም ባለመጣጣር ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል።
ማብዛትን፣ ኩራትን፣ ልቆ መታየትን፣ ከአቅም በላይ መጣጣርን አስቦ ከመናገር መከልከሉን እንረዳለን።
ሱነን ቲርሚዚ (3/ 545) (2018).
ተጨማሪ (4)
بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.
لسليم الهلالي (1/ 676).
تحفة الأحوذي.
للمباركفوري (6/ 135).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
6 መጻሕፍትተጨማሪ (6)
- الحقيقة المُبْهِرَة في العلاقة بين الإسلام والإنسان(إنّ من أحبكم إليَّ وأقربكم مني مجلساً يوم القيامة؛ أحاسنكم أخلاقاً)[130].
- دين الإسلام تعرضه نصوص القرآن وسنة خير الأنامعرض دين الإسلام بالأدلة النقلية(إن من أحبكم إليّ وأقربكم مني مجلساً يوم القيامة أحاسنكم أخلاقاً)[15]
- كتاب تعليم المسلم الجديد«إِنَّ مِنْ أَحَبِّكُمْ إِلَيَّ وَأَقْرَبِكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ، أَحَاسِنُكُمْ أَخْلَاقًا»
- مجموعة زاد الحديث (1)الحديث 1«إِنَّ مِنْ أَحَبِّكُمْ إِلَيَّ وَأَقْرَبِكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ القِيَامَةِ أَحَاسِنَكُمْ أَخْلَاقًا»
- نبراس طالب (1)1«إِنَّ مِنْ أَحَبِّكُمْ إِلَيَّ وَأَقْرَبِكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَحَاسِنَكُمْ أَخْلَاقًا»
- نبراس طالب (5)1«إِنَّ مِنْ أَحَبِّكُمْ إِلَيَّ وَأَقْرَبِكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَحَاسِنَكُمْ أَخْلَاقًا»