"አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ" አሉ። እርሳቸውም "በአስቸጋሪ ወቅት ዉዱእን አዳርሶ ማድረግ፣ ወደ መስጂድ እርምጃ ማብዛት፣ አንድ ሰላት ካለቀ በኋላ ሌላ ሶላት መጠበቅ፤ ይኸው ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ) ናቸው።"
«أَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى مَا يَمْحُو اللهُ بِهِ الْخَطَايَا، وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟» قَالُوا بَلَى يَا رَسُولَ اللهِ قَالَ: «إِسْبَاغُ الْوُضُوءِ عَلَى الْمَكَارِهِ، وَكَثْرَةُ الْخُطَا إِلَى الْمَسَاجِدِ، وَانْتِظَارُ الصَّلَاةِ بَعْدَ الصَّلَاةِ، فَذَلِكُمُ الرِّبَاطُ».
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለወንጀሎቻቸው መማር፣ ከጠባቂ መልአክት መዝገብ ወንጀላቸውን ለማሰረዝ፣ በጀነት ውስጥም ደረጃዎችን ከፍ ለማድረግ ምክንያት የሚሆኑ ስራዎችን እንዲጠቁሟቸው ይፈልጉ እንደሆነ ባልደረቦቻቸውን ጠየቋቸው። ሶሐቦችም: "አዎን እንፈልጋለን" አሉ። እሳቸውም እንዲህ አሉ: የመጀመሪያው: እንደ ቅዝቃዜ፣ የውሃ ማነስ፣ የሰውነት ህመምና አቃጣይ ውሃን የመሰሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም ዉዱእን መሙላትና ማዳረስ ነው። ሁለተኛው: ከሩቅ አካባቢ በመነሳት ወደ መስጂድ እርምጃን ማብዛትና ደጋግሞ መመላለስ ነው። ሶስተኛ: የሶላትን ወቅት መጠበቅ፣ ልብን በሶላት ማንጠልጠል፣ ለሶላት መዘጋጀት፣ ጀመዓን ለመጠበቅ መስጂድ ውስጥ ለሶላት መቀመጥ፣ ከሰገደም በኋላ ለሌላ ሶላት መስገጃው ላይ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ነው። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህ ጉዳዮች ትክክለኛው ዘብ መጠበቅ እንደሆኑ ገለፁ። ምክንያቱም የሰይጣንን መንገዶች በነፍስ ላይ ስለምትዘጋ፣ ስሜትን ስለምታሸንፍ፣ ነፍስ ለወስዋስ ተገዥ እንዳትሆን ስለምትከለክል ነው። ነፍስን በማሸነፍ የአላህ ጭፍራ የሰይጣንን ሰራዊት ያሸንፉበታል። ትልቁ ጂሀድም ይህ ነው። ስለዚህ የዚህ ደረጃ ኬላ ላይ ጠላትን እንደመጠበቅ እንደሆነ አድርገው ገለፁት።
መስጂድ ውስጥ የህብረት ሶላትን የመጠባበቅ አንገብጋቢነቱን፣ ለሶላት ትኩረት መስጠትና ከሶላት በሌላ ነገር መጠመድ እንደሌለብንም እንረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስራው የሚያስገኘውን ትልቅ ምንዳ በጥያቄያዊ መንገድ አስቀድመው ባልደረቦቻቸውን ማጓጓታቸው የትምህርት አቀራረባቸውን ማማር እንረዳለን። ይህም አንዱ የማስተማሪያ መንገድ ነው።
አንድን ጉዳይ በጥያቄና መልስ መንገድ ማቅረብ ብይኑን መጀመሪያ በመደበቅና ቀጥሎ በማብራራት ንግግሩ ነፍስ ውስጥ እንዲቀር የማድረግ ጥቅም አለው።
ነወዊይ አላህ ይዘንላቸውና «ይህ ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ)» ማለት ተፈላጊው ዘብ መጠበቅ ይህ ነው ማለት ነው። ሪባጥ የሚለው ቃል መሰረት በአንድ ነገር ላይ መታጠር ማለት ሲሆን በነዚህ ስራዎች አላህን በመገዛት ላይ ነፍሱን ስለሚያጥር ነው። "ጂሃድ ማለት ነፍስን መታገል ነው።" እንደሚባለው በላጩ ሪባጥ ይህ ነውም ተብሏል። በሌላ አባባል ደሞ ቀላሉና የሚመቸው ሪባጥ ነው ማለት ተፈልጎበት ሊሆንም ያስመቻል። ማለትም ከሪባጥ አይነቶች አንዱ ነው እንደማለት ነው።
(አል) የምትለዋ ገላጭ ገብታ "አር‐ሪባጥ" የምትለዋ ቃል መደጋገሟ የነዚህ ስራዎችን ትልቅነት ያስረዳናል።
ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 219) (251).
ተጨማሪ (8)
كنوز رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين.
شرح رياض الصالحين.
لابن عثيمين (2/ 183).
بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.
لسليم الهلالي (1/ 209).
نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.
لمجموعة من الباحثين (1/ 158).
በመጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሰ
10 መጻሕፍትተጨማሪ (10)
- الخطب المنبرية موسوعة الخطب المنبرية (القسم الثاني)«أَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى مَا يَمْحُو اللَّهُ بِهِ الخَطَايَا وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟» قَالُوا: بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ. قَالَ: «إِسْبَاغُ الوُضُوءِ عَلَى المَكَارِهِ، وَكَثْرَةُ الخُطَى إِلَى المَسَاجِدِ، وَانْتِظَارُ الصَّلَاةِ بَع
- الصلاة التي علمها النبي ﷺ الصحابة رضي الله عنهمالصلاة التي علمها النبي ﷺ الصحابة رضي الله عنهم«أَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى مَا يَمْحُو اللَّهُ بِهِ الْخَطَايَا، وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟» قَالُوا: بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ. قَالَ: «إِسْبَاغُ الْوُضُوءِ عَلَى الْمَكَارِهِ، وَكَثْرَةُ الْخُطَا إِلَى الْمَسَاجِدِ، وَانْتِظَارُ الصَّلَا
- الصلاة التي علمها النبي ﷺ الصحابة رضي الله عنهم«أَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى مَا يَمْحُو اللَّهُ بِهِ الْخَطَايَا، وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟» قَالُوا: بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ، قَالَ: «إِسْبَاغُ الْوُضُوءِ عَلَى الْمَكَارِهِ، وَكَثْرَةُ الْخُطَا إِلَى الْمَسَاجِدِ، وَانْتِظَارُ الصَّلَا
- المناهج التعليمية - الصف الرابعالمناهج التعليمية - الصف الرابع - الفقه«ألا أَدُلُّكُم على ما يَـمْحُو اللهُ بهِ الخطايا ويَرْفَع بِه الدَّرجات؟» قالوا: بلى يا رَسولَ اللهِ. قال: «إِسْبَاغُ الوُضُوءِ عَلَى الْمَكَارِهِ [3]، وَكَثْرَةُ الْخُطَىٰ إِلَى الْمَسَاجِدِ وَانْتِظَارُ الصَّلَاةِ بَعْدَ الصَّلَاةِ، فَذَ
- المنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح - المعتمدالمنتقى من المتجر الرابح في ثواب العمل الصالح“ألا أدلكم على ما يمحو الله به الخطايا ويرفع به الدرجات، قالوا: بلى يا رسول الله، قال: “إسباغ الوضوء على المكاره، وكثرة الخطا إلى المساجد، وانتظار الصلاة بعد الصلاة، فذلكم الرباط “
- الميسر في صفة الوضوء"ألا أدلُّكم على ما يمحو الله به الخطايا، ويرفع به الدرجات؟"،
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 1 «ألا أَدلُّكُمْ عَلَىٰ مَا يَمْحُو اللهُ بِهِ الْخَطَايَا، وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟»
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 5«ألا أدُلُّكُم علىٰ مَا يَمْحُو اللهُ به الخَطَايَا، ويرفعُ به الدَّرجاتِ؟»
- رياض الصالحينرياض الصالحين مع فوائد وهدايات - 5«أَلاَ أَدلُّكُمْ عَلىٰ مَا يَمْحُو اللهُ بِهِ الخَطَايَا، وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟»
- نبراس طالب (2)نبراس طالب (2) «أَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى مَا يَمْحُو اللهُ بِهِ الْخَطَايَا، وَيَرْفَعُ بِهِ الدَّرَجَاتِ؟» قَالُوا: بَلَى يَا رَسُولَ اللهِ. قَالَ: «إِسْبَاغُ الْوُضُوءِ عَلَى الْمَكَارِهِ([2])، وَكَثْرَةُ الْخُطَا إِلَى الْمَسَاجِدِ، وَانْتِظَارُ الصَّلَ