Skip to content

"ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!"

ዐምር ቢን ሹዐይብ ከአባቱ፣ አባቱም ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:

"ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!"

«مُرُوا أولادكمِ بالصلاةِ وهم أبناءُ سبعِ سِنينَ، واضرِبوهم عليها وهم أبناءُ عَشرٍ، وفرِّقوا بينهم في المَضاجِعِ».

አቡዳውድ ዘግበውታል።
ሐሰን ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አባት ወንድና ሴት ልጆቹን ገና ሰባት ዓመት እያሉ ሶላት እንዲሰግዱ ማዘዝና ሶላትን በማስተካከል ላይ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ማስተማር እንዳለበት ገለፁ። አስር ዓመት የደረሱ ጊዜም ትእዛዙን ይጨምራል። ሶላትን በማጓደላቸው ይመታቸዋልም በመኝታ ስፍራም በመካከላቸው ይለያያቸዋል።

የቃላት ፍቺ

...:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

ህፃናት ልጆችን አቅመ አዳም ከመድረሳቸውም በፊት የዲን ጉዳዮችን ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን። ከአንገብጋቢዎቹ መካከልም አንዱ ሶላት ነው።

መምታቱ ለሥርዓት (ለማስተማር) እንጂ ለመቅጣት አይደለምና ሁኔታውን በሚመጥን መልኩ መቅጣት ይገባል።

ሸሪዓ ክብርን ለመጠበቅ የሰጠውን ትኩረትና ወደ ብክለት የሚያደርስን መንገድ ሁሉ መዝጋቱን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሱነን አቡዳውድ (1/ 367) (495.

496).

ተጨማሪ (4)

نزهة المتقين شرح رياض الصالحين.

مجموعة من الباحثين (1/ 299).

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (1/ 382).