Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የአላህ ነቢይ ሆይ! ሐቃቸውን የሚጠይቁ ሐቃችንን ደግሞ የሚከለክሉን መሪዎች በኛ መካከል ቢመጡ ምን ያዙናል እስኪ ንገሩን?" እርሳቸውም ከርሱ ዘወር አሉ። እርሱም ድጋሚ ጠየቃቸው እርሳቸው ግን አሁንም ከርሱ ዘወር አሉ። እርሱም በድጋሚ ለሁለተኛ ወይም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቃቸው። በዚህ ጊዜ አሽዐሥ ቢን ቀይስ ጎተተው። እርሳቸውም "መሪያችሁን ስሙ ታዘዙም! በነርሱ ላይ የተሸከሙት ግዴታ አለባቸው። በናንተም ላይ የተሸከማችሁት ግዴታ አለባችሁ።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁን) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።' አሏቸው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"አላህን በመፍራት፤ ባሪያ እንኳ ቢሾምባችሁ እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። እነሆ! ከናንተ መካከል ከኔ በኋላ የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ማየቱ አይቀርም፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።" አሏቸው።»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ሃይማኖት (ኢስላም) መቆርቆር (ታማኝነት) ነው።" እኛም "ለማን ነው (የምንቆረቆረው) ታማኝ የምንሆነው?" አልናቸው። እሳቸውም "ለአላህ፣ ለመጽሐፉ፣ ለመልክተኛው፣ ለሙስሊሞች መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም። ወደኔ ምንጭም (ወደ ሐውድ) አይመጣም። የነርሱን ውሸት አምኖ ያልተቀበለና በበደላቸውም ላይ ያላገዛቸው ሰው ደሞ እርሱ ከኔ ነው። እኔም ከርሱ ነኝ። ወደኔ ምንጭ (ሐውድም) ይመጣል።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።