Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 9 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"መሃላ ሸቀጥን ተፈላጊ የሚያደርግ (የሚያዋድድ)፤ ትርፍን (በረከት) ደግሞ የሚያጠፋ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህ አለ: ‹የአደም ልጅ ዘመንን በመሳደብ ያውከኛል። ዘመን እኔው ነኝ ፤ ነገሮች በኔ እጅ ናቸው፤ ምሽቱንና ቀኑን የምገለባብጠው እኔ ነኝ።›"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።" አሉ። "የምናገረው ነገር ወንድሜ ላይ ካለስ (ሀሜት ይባላልን?)" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም "የምትናገረው ነገር እሱ ላይ ካለ በርግጥ አምተኸዋል። እሱ ላይ ከሌለ ደግሞ በርግጥም ቀጥፈህበታል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! መዳኛ ምንድን ነው? አልኳቸው። እርሳቸውም "ምላስህን ተቆጣጠር፤ ቤትህ ይስፋህ፤ በወንጀልህም ላይ አልቅስ!" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።"»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ማንኛውም ለወንድሙ ‹አንተ ከሀዲ› ያለ ሰው በርግጥም በርሷ (በከሀዲነቷ) ላይ አንዳቸው ወድቀዋል። እንዳለው ሆኖ ከሆነ (መልካም) ያለበለዚያ ወደርሱ ትመለሳለች።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።